ከአሀዋ ወንዝ ተነሥተን ወደ ኢየሩሳሌም ጒዞ የጀመርነውም የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ነበር፤ በምንጓዝበትም ጊዜ አምላካችን ከእኛ ጋር ስለ ነበር ከጠላት አደጋና ከደፈጣ ተዋጊዎች ሽመቃ ጠበቀን።
ሐዋርያት ሥራ 20:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያም ሦስት ወር ቈየ፤ ከዚህ በኋላ በመርከብ ወደ ሶርያ ለመሄድ አሰበ፤ ግን አይሁድ በእርሱ ላይ ሤራ ማድረጋቸውን ባወቀ ጊዜ በመቄዶንያ በኩል ለመመለስ ወሰነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ሦስት ወር ተቀመጠ። ወደ ሶርያ በመርከብ ለመሄድ ሲዘጋጅም አይሁድ አሢረውበት ስለ ነበር፣ በመቄዶንያ በኩል አድርጎ ለመመለስ ወሰነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ሦስት ወር ተቀምጦ ወደ ሶርያ በመርከብ ሊሄድ ባሰበ ጊዜ፥ አይሁድ ሤራ ስላደረጉበት በመቄዶንያ አልፎ ይመለስ ዘንድ ቆረጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ሦስት ወር ተቀመጠ፤ ወደ ሶርያም በመርከብ ለመሄድ ዐስቦ ሳለ አይሁድ ስለ ተማከሩበት ወደ መቄዶንያ ሊመለስ ቈረጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ሦስት ወር ተቀምጦ ወደ ሶርያ በመርከብ ሊሄድ ባሰበ ጊዜ፥ አይሁድ ሴራ ስላደረጉበት በመቄዶንያ አልፎ ይመለስ ዘንድ ቆረጠ። |
ከአሀዋ ወንዝ ተነሥተን ወደ ኢየሩሳሌም ጒዞ የጀመርነውም የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ነበር፤ በምንጓዝበትም ጊዜ አምላካችን ከእኛ ጋር ስለ ነበር ከጠላት አደጋና ከደፈጣ ተዋጊዎች ሽመቃ ጠበቀን።
“በሕዝቤ መካከል የሚኖሩ ክፉ ሰዎች አሉ፤ እነርሱም ወፎችን በወጥመድ እንደሚይዝ ሰው ናቸው፤ ስለዚህ ሰዎችን ለማጥመድ መረባቸውን ዘርግተው ያደባሉ።
ዝናው በሶርያ አገር ሁሉ ስለ ተሰማ፥ ሰዎች በልዩ ልዩ በሽታና ደዌ የሚሠቃዩትን፥ ርኩሳን መናፍስት ያደሩባቸውን፥ የሚጥል በሽታ ያለባቸውንና ሽባዎችንም ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።
ከዚያም ተነሥተን ወደ ፊልጵስዩስ ደረስን፤ ፊልጵስዩስ በመቄዶንያ የምትገኝ ታላቅ ከተማና የሮማውያን ቅኝ አገር ነበረች፤ በዚህችም ከተማ ጥቂት ቀኖች አሳለፍን።
ጳውሎስ ከወንድሞች ጋር ብዙ ቀኖች በቆሮንቶስ ከቈየ በኋላ ተሰናብቶአቸው ወደ ሶርያ ሄደ፤ ጵርስቅላና አቂላም ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ ነገር ግን ስለት ስለ ነበረበት ከመሄዱ በፊት ክንክሪያ በሚባል ቦታ ራሱን ተላጨ።
ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ጳውሎስ በመቄዶንያና በአካይያ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ በመንፈሱ አስቦ “እዚያ ከደረስኩ በኋላ ወደ ሮም መሄድ አለብኝ” አለ።
በጒዞዬ ብዛት የወንዝና የጐርፍ፥ የሽፍቶችም አደጋ ደርሶብኛል፤ ከአይሁድ ወገኖቼና ከአሕዛብ አደጋ ደርሶብኛል፤ በከተማና በበረሓ በባሕርም አደጋ ደርሶብኛል፤ እንዲሁም ከሐሰተኞች አማኞች አደጋ ደርሶብኛል።