ሐዋርያት ሥራ 19:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ርኩስ መንፈስ ያደረበትም ሰው ዘሎ በማነቅ በረታባቸው፤ አሸነፋቸውም፤ ቈስለውና ራቊታቸውን ሆነው ከቤት ሸሽተው ወጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ርኩስ መንፈስ ያደረበት ሰው ዘልሎ ያዛቸው፤ በረታባቸውም፤ እጅግ ስላየለባቸውም ቤቱን ጥለው ዕራቍታቸውን ሸሹ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉው መንፈስም ያለበት ሰው ዘለለባቸው፤ ቆስለውም ከዚያ ቤት ዕራቁታቸውን እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው፤ አሸነፋቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያም ክፉ መንፈስ የያዘው ሰው ተነሣባቸው፤ አየለባቸውም፤ አሸነፋቸውም፤ አቍስሎም ከዚያ ቤት አስወጥቶ አባረራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክፉው መንፈስም ያለበት ሰው ዘለለባቸው ቆስለውም ከዚያ ቤት ዕራቁታቸውን እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው አሸነፋቸውም። |
ይህንንም ያለበት ምክንያት ኢየሱስ ርኩሱን መንፈስ ከሰውየው እንዲወጣ አዞት ስለ ነበር ነው። ከዚህ በፊት ርኩሱ መንፈስ በሰውየው ላይ ብዙ ጊዜ ይነሣበት ነበር፤ በሰንሰለትና በእግር ብረት እየታሰረ ይጠበቅ ነበር፤ ይሁን እንጂ ሰንሰለቱን ይበጥስ፥ እግር ብረቱንም ይሰብር ነበር። ጋኔኑም እየነዳ ወደ በረሓ ይወስደው ነበር።
ሰዎቹም የሆነውን ነገር ለማየት ከየቤታቸው ወጥተው ወደ ኢየሱስ መጡ፤ አጋንንት የወጡለትንም ሰው ልቡናው ተመልሶለትና ልብሱንም ለብሶ በኢየሱስ እግር ሥር ተቀምጦ ባዩት ጊዜ ፈሩ፤