እኔም በደኅና እስክመለስ ድረስ በእስር ቤት አስገብተው ደረቅ እንጀራና ውሃ ብቻ እየሰጡት እንዲቈይ ያደርጉ ዘንድ በእኔ ስም ንገራቸው” ሲል አዘዘው።
ሐዋርያት ሥራ 16:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠባቂው ይህን ትእዛዝ ከተቀበለ በኋላ፥ በወህኒ ቤቱ ውስጠኛ ክፍል አስገባቸው፤ እግሮቻቸውንም በግንድና ግንድ መካከል አጣብቆ አሰራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ይህን የመሰለ ትእዛዝ ከተቀበለ በኋላ፣ ወደ ወህኒ ቤቱ ውስጠኛ ክፍል አስገብቶ እግራቸውን ከግንድ ጋራ አጣብቆ አሰራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም የዚህን ዓይነት ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ጣላቸው፤ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ትእዛዙን ተቀብሎ ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ቤት አስገባቸው፤ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም የዚህን ዓይነት ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ጣላቸው፥ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸ። |
እኔም በደኅና እስክመለስ ድረስ በእስር ቤት አስገብተው ደረቅ እንጀራና ውሃ ብቻ እየሰጡት እንዲቈይ ያደርጉ ዘንድ በእኔ ስም ንገራቸው” ሲል አዘዘው።
ይህ አነጋገር አሳን እጅግ ስላስቈጣው ነቢዩን በብረት ሰንሰለት አስሮ ወህኒ አስገባው፤ ከዚህም ጊዜ አንሥቶ፥ ንጉሥ አሳ ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶቹን በጭካኔ ማንገላታት ጀመረ።
“እግዚአብሔር በካህኑ በዮዳሄ ቦታ ካህን አድርጎ ሾሞሃል፤ እነሆ የቤተ መቅደሱም የበላይ አለቃ አንተ ነህ፤ ስለዚህም ነቢይ ነኝ እያለ በማስመሰል የሚናገረውን አንዳንድ ዕብድ በአንገት ሰንሰለትና በእግር ግንድ እየጠፈሩ ማሰር የአንተ ተግባር መሆን አለበት፤
ስለዚህም እኔን ይዘው በቤተ መንግሥቱ አደባባይ በሚገኘው ወደ ንጉሥ ልጅ ወደ መልክያ የውሃ ጒድጓድ ውስጥ በገመድ ቊልቊል በመልቀቅ ወደ ታች አወረዱኝ፤ በጒድጓዱም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውሃ አልነበረበትም፤ እኔም በጭቃው ውስጥ ሰመጥሁ።