ስለዚህም ሃማን ለንጉሥ አርጤክስስ እንዲህ ሲል አስረዳው፦ “በንጉሠ ነገሥት መንግሥትህ ግዛት ውስጥ በየአገሩ ተበታትኖ የሚኖር አንድ ሕዝብ አለ፤ ይህም ሕዝብ ከሌሎች አሕዛብ የተለየ ሕግ አለው፤ ከዚህም በላይ ለንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ሕግ ታዛዥ ሆኖ አልተገኘም፤ ታዲያ፥ ይህን ዐይነቱን ሕዝብ ዝም ብለህ ብትታገሥ ለአንተ አደገኛ ነገር ይሆንብሃል፤
ሐዋርያት ሥራ 16:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ የሮም ዜጋዎች ልንቀበለው ወይም ልናደርገው ያልተፈቀደልንን ሥርዓት ያስተምራሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም እኛ ሮማውያን መቀበል ወይም መፈጸም ያልተፈቀደልንን ልማድ በሕዝቡ መካከል ይነዛሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛም የሮሜ ሰዎች ሆነን እንቀበላቸውና እናደርጋቸው ዘንድ ያልተፈቀደልንን ልማዶች ይናገራሉ፤” አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛ የሮሜ ሰዎች ስንሆንም ልናደርገው የማይገባንን ሕግ ይናገራሉ” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛም የሮሜ ሰዎች ሆነን እንቀበላቸውና እናደርጋቸው ዘንድ ያልተፈቀደልንን ልማዶች ይናገራሉ” አሉ። |
ስለዚህም ሃማን ለንጉሥ አርጤክስስ እንዲህ ሲል አስረዳው፦ “በንጉሠ ነገሥት መንግሥትህ ግዛት ውስጥ በየአገሩ ተበታትኖ የሚኖር አንድ ሕዝብ አለ፤ ይህም ሕዝብ ከሌሎች አሕዛብ የተለየ ሕግ አለው፤ ከዚህም በላይ ለንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ሕግ ታዛዥ ሆኖ አልተገኘም፤ ታዲያ፥ ይህን ዐይነቱን ሕዝብ ዝም ብለህ ብትታገሥ ለአንተ አደገኛ ነገር ይሆንብሃል፤
ከዚያም ተነሥተን ወደ ፊልጵስዩስ ደረስን፤ ፊልጵስዩስ በመቄዶንያ የምትገኝ ታላቅ ከተማና የሮማውያን ቅኝ አገር ነበረች፤ በዚህችም ከተማ ጥቂት ቀኖች አሳለፍን።