ሐዋርያት ሥራ 14:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጳውሎስና በርናባስ በደርቤ ወንጌልን አስተምረው ብዙ ሰዎችን አማኞች ካደረጉ በኋላ በልስጥራና በኢቆንዮን አልፈው በጵስድያ ወደምትገኘው አንጾኪያ ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጳውሎስና በርናባስ በደርቤን የምሥራቹን ቃል ሰብከው፣ ብዙ ደቀ መዛሙርትም ካፈሩ በኋላ፣ ወደ ልስጥራን፣ ወደ ኢቆንዮንና ወደ አንጾኪያ ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያችም ከተማ ወንጌልን ሰብከው እጅግ ደቀ መዛሙርትን ካደረጉ በኋላ፥ የደቀ መዛሙርትን ልብ እያጸኑ በሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ እየመከሩና “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል፤” እያሉ፥ ወደ ልስጥራን ወደ ኢቆንዮንም ወደ አንጾኪያም ተመለሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያችም ከተማ ወንጌልን ሰበኩ፤ ብዙ ሰዎችንም ደቀ መዛሙርት አድርገው ወደ ልስጥራን፥ ወደ ኢቆንዮንና ወደ አንጾኪያ ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያችም ከተማ ወንጌልን ሰብከው እጅግ ደቀ መዛሙርትን ካደረጉ በኋላ፥ የደቀ መዛሙርትን ልብ እያጸኑ በሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ እየመከሩና፦ “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል” እያሉ፥ ወደ ልስጥራን ወደ ኢቆንዮንም ወደ አንጾኪያም ተመለሱ። |
በኢቆንዮን ጳውሎስና በርናባስ አብረው ወደ አይሁድ ምኲራብ ገቡ፤ በዚያም ብዙ አይሁድና ከአሕዛብ እጅግ ብዙ ሰዎች እስኪያምኑ ድረስ አስተማሩ።
“እናንተ ሰዎች ለምን ይህን ታደርጋላችሁ? እኛም እንደ እናንተ ሰዎች ነን፤ እኛ እዚህ የመጣነው እናንተ ከዚህ ከከንቱ ነገር ሁሉ ርቃችሁ ሰማይን፥ ምድርን፥ ባሕርንና በውስጣቸው የሚገኙትን ሁሉ ወደ ፈጠረው ወደ ሕያው አምላክ እንድትመለሱ መልካም ዜና ልናበሥርላችሁ ነው፤
አይሁድ ግን ከአንጾኪያና ከኢቆንዮን ወደዚያ መጥተው ሕዝቡን አሳደሙና ጳውሎስን በድንጋይ እንዲወግሩት አደረጉ፤ የሞተ መስሎአቸውም ጐትተው ከከተማ አወጡት።
ከጥቂት ቀኖች በኋላ ጳውሎስ በርናባስን “ና እንመለስና ከዚህ በፊት የጌታን ቃል ባበሠርንባቸው ከተሞች ሁሉ ያሉትን ወንድሞች እንጐብኝ፤ እንዴት እንደ ሆኑም እንወቅ” አለው።
እንዲሁም ስደቴንና መከራዬን ታውቃለህ፤ በአንጾኪያና በኢቆንዮን በልስጥራንም የደረሰብኝን ነገርና በትዕግሥት የተቀበልኩትንም ስደት ታውቃለህ፤ ጌታ ግን ከሁሉም አዳነኝ።