እዚያም እንደ ደረሱ አባታቸውን “ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ እንዲያውም በመላው ግብጽ ላይ አስተዳዳሪ ሆኖአል” አሉት። ያዕቆብ ግን እጅግ ደነገጠ፤ ሊያምናቸውም አልቻለም።
ሐዋርያት ሥራ 12:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጴጥሮስም ወጣና ተከተለው፤ ራእይ የሚያይ መሰለው እንጂ መልአኩ ያደረገው ነገር ሁሉ እውነት አልመሰለውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጴጥሮስም ተከትሎት ከእስር ቤት ወጣ፤ ነገር ግን ራእይ የሚያይ መሰለው እንጂ መልአኩ የሚያደርገው ነገር በእውን መሆኑን አላወቀም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ልብስህንም ልበስና ተከተለኝ፤” አለው። ወጥቶም ተከተለው፤ ራእይንም የሚያይ ይመስለው ነበር እንጂ በመልአኩ የሚደረገው ነገር እውነት እንደሆነ አላወቀም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተከትሎትም ወጣ፤ ጴጥሮስ ግን ራእይ የሚያይ ይመስለው ነበረ እንጂ በመልአኩ የሚደረገው ነገር እውነት እንደ ሆነ አላወቀም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “ልብስህንም ልበስና ተከተለኝ” አለው። ወጥቶም ተከተለው፤ ራእይንም የሚያይ ይመስለው ነበር እንጂ በመልአኩ የሚደረገው ነገር እውነት እንደ ሆነ አላወቀም። |
እዚያም እንደ ደረሱ አባታቸውን “ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ እንዲያውም በመላው ግብጽ ላይ አስተዳዳሪ ሆኖአል” አሉት። ያዕቆብ ግን እጅግ ደነገጠ፤ ሊያምናቸውም አልቻለም።
ጴጥሮስ የራእዩ ፍች “ምን ይሆን?” እያለ በሐሳቡ ሲጨነቅ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች በጥያቄ የስምዖንን ቤት አግኝተው በበር ቆመው ነበር፤
“እኔ በኢዮጴ ከተማ በጸሎት ላይ ሳለሁ በተመስጦ ራእይ አየሁ፤ ያየሁትም ትልቅ የመጋረጃ ጨርቅ የሚመስል ነገር በአራት ማእዘን ተይዞ ከሰማይ ሲወርድና ወደ እኔ ሲመጣ ነው፤
በዚያን ጊዜ በደማስቆ ሐናንያ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበር፤ ጌታ በራእይ “ሐናንያ!” ብሎ ጠራው፤ እርሱም “እነሆኝ ጌታ ሆይ!” አለ።
አብርሃም ወጥቶ ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ ምንም እንኳ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም ለመሄድ የታዘዘው በእምነት ነው።