ሐዋርያት ሥራ 11:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ሁለተኛ ጊዜ፥ ‘እግዚአብሔር ንጹሕ ያደረገውን አንተ ርኩስ ነው ማለት አይገባህም’ የሚል መልስ ከሰማይ ሰማሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ያም ድምፅ ለሁለተኛ ጊዜ፣ ‘እግዚአብሔር ንጹሕ ያደረገውን አንተ እንደ ርኩስ አትቍጠረው’ ሲል ከሰማይ ተናገረኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለተኛም ‘እግዚአብሔር ያነጻውን አንተ አታርክሰው፤’ የሚል ድምፅ ከሰማይ መለሰልኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም፦ ‘እግዚአብሔር ንጹሕ ያደረገውን አንተ አታርክሰው’ የሚል ቃል ከሰማይ መለሰልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለተኛም፦ “እግዚአብሔር ያነጻውን አንተ አታርክሰው” የሚል ድምፅ ከሰማይ መለሰልኝ። |
እንዲህም አላቸው፦ “አይሁዳዊ ለሆነ ሰው ከሌላ ሕዝብ ጋር ለመተባበርና ወደ ቤቱም ለመግባት በሃይማኖታችን ሕግ እንደማይፈቀድ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ፤ ነገር ግን ማንንም ንጹሕ ያልሆነ ወይም ርኩስ እንዳልል እግዚአብሔር ገልጦልኛል።