“በዚያን ጊዜ ተራራዎችም ሁሉ በወይን ተክል ይሸፈናሉ፤ በኰረብቶችም ላይ ብዙ ወተት የሚሰጡ ከብቶች ይሰማራሉ፤ በይሁዳ ምድር የሚገኙ ወንዞች ሁሉ በውሃ የተሞሉ ይሆናሉ፤ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ምንጭ ይፈልቃል፤ የሺጢምንም ሸለቆ ያጠጣል።
ሐዋርያት ሥራ 1:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሐንስ በውሃ አጠመቀ፤ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሐንስ በውሃ አጥምቆ ነበርና፣ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሐንስ በውሃ አጥምቆ ነበርና፤ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ፤” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዮሐንስ በውኃ አጠመቀ፤ እናንተ ግን እስከ ቅርብ ቀን ድረስ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፥ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኃላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ” አለ። |
“በዚያን ጊዜ ተራራዎችም ሁሉ በወይን ተክል ይሸፈናሉ፤ በኰረብቶችም ላይ ብዙ ወተት የሚሰጡ ከብቶች ይሰማራሉ፤ በይሁዳ ምድር የሚገኙ ወንዞች ሁሉ በውሃ የተሞሉ ይሆናሉ፤ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ምንጭ ይፈልቃል፤ የሺጢምንም ሸለቆ ያጠጣል።
እነሆ፥ እኔ ለንስሓ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፤ እርሱ ከእኔ እጅግ ይበልጣል፤ እኔ የእግሩን ጫማ እንኳ ለመሸከም የተገባሁ አይደለሁም።
ዮሐንስ ግን ለሁሉም እንዲህ አላቸው፦ “እኔ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ነገር ግን ሌላ ከእኔ የሚበረታ ይመጣል፤ እኔ የእርሱን ጫማ ማሰሪያ ለመፍታት እንኳ የበቃሁ አይደለሁም፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል።
እኔ ራሴ አላውቀውም ነበር፤ ነገር ግን በውሃ እንዳጠምቅ የላከኝ፥ ‘መንፈስ ቅዱስ ሲወርድና በእርሱ ላይ ሲያርፍበት የምታየው በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቅ እርሱ ነው’ ሲል ነግሮኛል።
ጳውሎስም “የዮሐንስ ጥምቀትማ ንስሓ ስለ መግባት የተፈጸመ ነው፤ ለሕዝቡም የተናገረው ‘ከእኔ በኋላ በሚመጣው እመኑ’ እያለ ነበር፤ እርሱም ኢየሱስ ነው” አላቸው።
አይሁድም ብንሆን የግሪክ ሰዎች ብንሆን፤ ባሪያዎችም ብንሆን፥ ነጻ ሰዎችም ብንሆን፥ አንድ ሰውነት ለመሆን በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀናል፤ ሁላችንም ከዚሁ ከአንዱ መንፈስ ጠጥተናል።
እኛ በሠራነው የጽድቅ ሥራ ሳይሆን ራሱ በምሕረቱ አዳነን፤ ያዳነንም በአዲስ ልደት መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በተገኘው መታደስ ነው።