ሐዋርያት ሥራ 1:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቴዎፍሎስ ሆይ! በመጀመሪያ መጽሐፌ ኢየሱስ የሠራውንና ያስተማረውን ሁሉ ጽፌአለሁ። የጻፍኩትም ኢየሱስ ሥራውን ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቴዎፍሎስ ሆይ፤ ኢየሱስ ለማድረግና ለማስተማር የጀመረውን ሁሉ ቀደም ባለው መጽሐፌ ጽፌልሃለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቴዎፍሎስ ሆይ! ኢየሱስ የመረጣቸውን ሐዋርያትን በመንፈስ ቅዱስ ካዘዛቸው በኋላ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ፥ ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ ስለ ጀመረው ሁሉ መጀመሪያውን ነገር ጻፍሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሊያደርገውና ሊያስተምረው የጀመረውን ሥራ ሁሉ አስቀድሜ በመጽሐፍ ጽፌልሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ኢየሱስ የመረጣቸውን ሐዋርያትን በመንፈስ ቅዱስ ካዘዛቸው በኋላ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ፥ ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ ስለ ጀመረው ሁሉ መጀመሪያውን ነገር ጻፍሁ፤ |
ኢየሱስም “ምንድን ነው እርሱ?” አላቸው። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦ “በናዝሬቱ ኢየሱስ ላይ ስለ ተፈጸመው ነገር ነዋ! እርሱ በእግዚአብሔርና በሰዎች ሁሉ ፊት በቃልና በሥራ ብርቱ የሆነ ነቢይ ነበር።
ኢየሱስ የማስተማር ሥራውን ሲጀምር፥ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያኽል ሆኖት ነበር፤ ለሕዝቡ ኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ ይመስላቸው ነበር፤ ይኸውም ዮሴፍ የዔሊ ልጅ፥
“የእስራኤል ሰዎች ሆይ! ይህን ቃል አዳምጡ፤ እናንተ ራሳችሁ እንደምታውቁት የናዝሬቱ የኢየሱስ ማንነት እግዚአብሔር በእናንተ መካከል በእርሱ አማካይነት በፈጸማቸው ታላላቅ ሥራዎች፥ ተአምራትና ምልክቶች ተረጋግጦአል።