3 ዮሐንስ 1:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእውነት ለማፈቅረው፥ ለተወደደው ጋይዮስ፥ ከእኔ ከሽማግሌው የተላከ መልእክት፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሽማግሌው፤ በእውነት ለምወድደው ለውድ ወዳጄ ለጋይዮስ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሽማግሌው፥ በእውነት ለምወደው ለተወደደው ለጋይዮስ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሽማግሌው በእውነት እኔ ለምወደው ለተወደደው ለጋይዮስ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሽማግሌው በእውነት እኔ ለምወደው ለተወደደው ለጋይዮስ። |
ከተማዋም በሙሉ ተሸበረች፤ ሕዝቡም የመቄዶንያ ተወላጆች የሆኑትን ሁለቱን የጳውሎስን የጒዞ ጓደኞች፥ ጋይዮስንና አርስጥሮኮስን ይዘው እየጐተቱ ወደ ሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታ ሮጡ።
የጲርሁስ ልጅ ሶጳጥሮስ ከቤርያ፥ አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ ከተሰሎንቄ፥ ጋይዮስ ከደርቤ፥ ጢሞቴዎስ፥ ቲኪቆስና ጥሮፊሞስ ከእስያ አብረውት ሄዱ።
እኔንና በዚህ ያለውን መላ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስተናግደው ጋይዮስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ የከተማይቱ በጅሮንድ የሆነው ኤራስጦስ፥ ወንድማችንም ቋርጦስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። [
እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር አብሬ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ የሆንኩ፥ የክርስቶስም መከራ ምስክር የሆንኩ፥ እንዲሁም ወደፊት የሚገለጠው ክብር ተካፋይ የምሆን፥ በመካከላችሁ ያሉትን የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ።