2 ጢሞቴዎስ 4:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለጵርስቅላና ለአቂላ፥ ለኦኔሲፎርም ቤተሰቦች ሰላምታ አቅርብልኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለጵርስቅላና ለአቂላ፣ ለሄኔሲፎሩም ቤተ ሰዎች ሰላምታ አቅርብልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጵርስቅላና ለአቂላ ለሄኔሲፎሩም ቤተሰቦች ሰላምታ አቅርብልኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለጵርስቅላና ለአቂላ ለሄኔሲፎሩም ቤተ ሰዎች ሰላምታ አቅርብልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለጵርስቅላና ለአቂላ ለሄኔሲፎሩም ቤተ ሰዎች ሰላምታ አቅርብልኝ። |
ጳውሎስ ከወንድሞች ጋር ብዙ ቀኖች በቆሮንቶስ ከቈየ በኋላ ተሰናብቶአቸው ወደ ሶርያ ሄደ፤ ጵርስቅላና አቂላም ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ ነገር ግን ስለት ስለ ነበረበት ከመሄዱ በፊት ክንክሪያ በሚባል ቦታ ራሱን ተላጨ።
እዚያ የጳንጦስ ተወላጅ የሆነውን አቂላ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ሰው አገኘ፤ የሮም ንጉሠ ነገሥት ቀላውዴዎስ አይሁድ ሁሉ ከሮም እንዲወጡ አዞ ስለ ነበረ አቂላ ከሚስቱ ከጵርስቅላ ጋር ከኢጣልያ ገና መምጣቱ ነበር፤ ስለዚህ ጳውሎስ ወደ እነርሱ ሄዶ ተዋወቃቸው፤
እርሱ በድፍረት በምኲራብ መናገር ጀመረ፤ ነገር ግን ጵርስቅላና አቂላ በሰሙት ጊዜ ወደ ቤታቸው ወሰዱትና የእግዚአብሔርን መንገድ ከፊት ይልቅ በትክክል አብራርተው ገለጡለት።
በእስያ ያሉ አብያተ ክርስቲያን ሰላምታ ያቀርቡላችኋል፤ አቂላና ጵርስቅላ፥ በቤታቸው የሚሰበሰቡ ክርስቲያኖችም ሁሉ ልባዊ ሰላምታ በጌታ ስም ያቀርቡላችኋል።