2 ጢሞቴዎስ 4:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቲኪቆስን ወደ ኤፌሶን ልኬዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቲኪቆስን ወደ ኤፌሶን ልኬዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቲኪቆስን ግን ወደ ኤፌሶን ላክሁት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቲኪቆስን ግን ወደ ኤፌሶን ላክሁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቲኪቆስን ግን ወደ ኤፌሶን ላክሁት። |
“እስከ አሁን በእናንተ ሁሉ መካከል እየተዘዋወርኩ የእግዚአብሔርን መንግሥት እሰብክ ነበር፤ ከእንግዲህ ወዲህ ግን ከእናንተ ማንም ከቶ ፊቴን እንደማያይ ዐውቃለሁ።
የጲርሁስ ልጅ ሶጳጥሮስ ከቤርያ፥ አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ ከተሰሎንቄ፥ ጋይዮስ ከደርቤ፥ ጢሞቴዎስ፥ ቲኪቆስና ጥሮፊሞስ ከእስያ አብረውት ሄዱ።
የተወደደው ወንድማችንና በጌታ ኢየሱስ ሥራ ታማኝ አገልጋይ የሆነው ቲኪቆስ የእኔ ሁኔታ እንዴት እንደ ሆነና ምን እንደምሠራ ሁሉን ነገር ይነግራችኋል።
ወደ መቄዶንያ ስሄድ ሳለሁ ዐደራ እንዳልኩህ እዚያ ያሉ አንዳንድ ሰዎች የሐሰት ትምህርት እንዳያስተምሩ ታደርጋቸው ዘንድ በኤፌሶን ተቀመጥ።
አርጤማስን ወይም ቲኪቆስን ወደ አንተ በምልክበት ጊዜ አንተ ወደ ኒቆጵልዮን ወደ እኔ ለመምጣት ፍጠን፤ እኔ ክረምቱን እዚያ ለማሳለፍ ወስኜአለሁ።