La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 8:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ንጉሥ ዳዊትም ድል ካደረጋቸው ከኤዶም፥ ከሞአብ፥ ከዐሞን፥ ከፍልስጥኤምና ከዐማሌቅ ከወሰደው ብርና ወርቅ፥ እንዲሁም ከሀዳድዔዜር ከወሰደው ምርኮ ጋር እነዚህንም ደግሞ ለእግዚአብሔር የተለዩ አደረገ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ንጉሥ ዳዊትም፣ ቀድሞ ካስገበራቸው መንግሥታት ሁሉ በገባለት ብርና ወርቅ እንዳደረገው፣ እነዚህንም ዕቃዎች ለእግዚአብሔር ቀደሳቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ንጉሥ ዳዊትም ቀድሞ ካስገበራቸው መንግሥታት ሁሉ በገባለት ብርና ወርቅ እንዳደረገው እነዚህንም ለጌታ ቀደሳቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱ​ንም ንጉሥ ዳዊት ከሀ​ገ​ሮች ሁሉ አም​ጥቶ ከቀ​ደ​ሰው ከወ​ር​ቁና ከብሩ ጋር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀደሰ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ንጉሥ ዳዊትም ካሸነፋቸው ከአሕዛብ ሁሉ ከሶርያ ከሞዓብም ከአሞንም ልጆች ከፍልስጥኤማውያንም ከአማሌቅም ከረአብም ልጅ ከሱባ ንጉሥ ከአድርአዛር ምርኮ ከቀደሰው ብርና ወርቅ ጋር እነዚህን ደግሞ ለእግዚአብሔር ቀደሰ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 8:11
8 Referencias Cruzadas  

ስለዚህም ንጉሥ ሀዳድዔዜርን ድል በመንሣቱ ሰላምታና የደስታ መግለጫ ያቀርብለት ዘንድ ልጁን ዮራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ ቀደም ሲልም ቶዒ በሀዳድዔዜር ላይ ጦርነት ሲያካሄድ የነበረ ነው፤ ዮራምም ከወርቅ፥ ከብርና ከነሐስ የተሠሩ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ለዳዊት ይዞለት ሄደ።


ንጉሥ ሰሎሞን የቤተ መቅደሱን ሥራ ሁሉ ከፈጸመ በኋላ አባቱ ዳዊት ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት እንዲውል የለየውን ብሩን፥ ወርቁንና ሌላውንም ዕቃ በሙሉ በቤተ መቅደሱ ግምጃ ቤት ውስጥ አኖረው።


ንጉሥ ዳዊትም እነርሱን ወስዶ ከኤዶም፥ ከሞአብ፥ ከዐሞን፥ ከፍልስጥኤምና ከዐማሌቅ ሕዝቦች ማርኮ ካመጣቸው ከወርቅ፥ ከብርና ከነሐስ ከተሠሩ ዕቃዎች ጋር ለአምልኮ ሥነ ሥርዓት መገልገያ እንዲሆኑ አደረጋቸው።


የምችለውን ያኽል፥ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ የሚሆኑትን ዕቃዎች ወርቅ ለወርቅ ሥራ፥ ብር ለብር ሥራ፥ ነሐስ ለነሐስ ሥራ፥ ብረት ለብረት ሥራ፥ እንጨት ለእንጨት ሥራ መርግድና የተለያዩ ቀለማት ያላቸው በፈርጥ የሚገቡ ድንጋዮች፥ የከበረ ድንጋይና በየዐይነቱ ብዙ ዕብነ በረድ አዘጋጅቼአለሁ።


ንጉሥ ሰሎሞን የቤተ መቅደሱን ሥራ ሁሉ ከፈጸመ በኋላ አባቱ ዳዊት ለእግዚአብሔር የተለዩ ያደረጋቸውን ብርና ወርቅ እንዲሁም ሌሎችን ዕቃዎች ሁሉ በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሚገኘው የዕቃ ግምጃ ቤት አኖራቸው።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እናንተ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! ሂዱና ጠላቶቻችሁን እንደ እህል አበራዩ! ቀንዱ ብረት፥ ሰኮናው ነሐስ እንደ ሆነ በሬ ብርቱ አደርጋችኋለሁ፤ ብዙ መንግሥታትን ትደመስሳላችሁ፤ እነርሱ በግፍ የሰበሰቡትን ሀብትና ንብረት ሁሉ ለመላው ዓለም ጌታ ለእኔ ለእግዚአብሔር አምጥታችሁ ታቀርባላችሁ።”