2 ሳሙኤል 6:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያም ሦስት ወር ተቀመጠ፤ እግዚአብሔርም ዖቤድኤዶምንና ቤተሰቡን ባረከ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርም ታቦት የጋት ሰው በሆነው በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀመጠ፤ እግዚአብሔርም አቢዳራንና ቤተ ሰቡን ሁሉ ባረከ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታም ታቦት የጌት ሰው በሆነው በዖቤድ ኤዶም ቤት ሦስት ወር ተቀመጠ፤ ጌታም ዖቤድ ኤዶምና ቤተሰቡን ሁሉ ባረከ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም ታቦት በጌት ሰው በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀመጠች፤ እግዚአብሔርም አቢዳራንና ቤቱን ሁሉ ባረከ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም ታቦት በጌት ሰው በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ያህል ተቀመጠ፥ እግዚአብሔርም አቢዳራንና ቤቱን ሁሉ ባረከ። |
እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ሆኖ የሚያደርገው ነገር ሁሉ እንዲቃናለት ስላደረገ የእስር ቤቱ አዛዥ በዮሴፍ ቊጥጥር ሥር በነበረው ነገር ምንም ሐሳብ አልነበረበትም።
ስለዚህም ታቦቱን ወደ ኢየሩሳሌም ላለመውሰድ ወሰነ፤ ይህንንም በማድረግ ፈንታ ከመንገድ መልሶ የጋት ከተማ ነዋሪ ወደ ሆነው ዖቤድኤዶም ተብሎ ወደሚጠራው ሰው ቤት አስገባው፤
ስምንት ወንዶች ልጆችን በመስጠት እግዚአብሔር የባረከው ዖቤድኤዶም የተባለም ሌላ ሰው ነበር፤ ልጆቹም በዕድሜአቸው ተራ ሸማዕያ፥ ይሆዛባድ፥ ዮአሕ፥ ሳካር፥ ናትናኤል፥
በቤተ መቅደሴ ሲሳይ ይበዛ ዘንድ ዐሥራቴን በሙሉ ወደ ጐተራ አግቡ፤ እናንተ ይህን ብታደርጉ እኔ ደግሞ የሰማይን መስኮቶች ከፍቼ መልካም የሆነውን በረከት ሁሉ አብዝቼ ባልሰጣችሁ በዚህ ልትፈትኑኝ ትችላላችሁ።