Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 26:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ስምንት ወንዶች ልጆችን በመስጠት እግዚአብሔር የባረከው ዖቤድኤዶም የተባለም ሌላ ሰው ነበር፤ ልጆቹም በዕድሜአቸው ተራ ሸማዕያ፥ ይሆዛባድ፥ ዮአሕ፥ ሳካር፥ ናትናኤል፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ዖቤድኤዶምም እንደዚሁ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ የመጀመሪያው ሸማያ፣ ሁለተኛው ዮዛባት፣ ሦስተኛው ኢዮአስ፣ አራተኛው ሣካር፣ ዐምስተኛው ናትናኤል፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ዖቤድ-ኤዶም ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም በኩሩ ሸማያ፥ ሁለተኛው ዮዛባት፥ ሦስተኛው ኢዮአስ፥ አራተኛው ሣካር፥ አምስተኛው ናትናኤል፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ዖቤ​ድ​ኤ​ዶ​ምም ልጆች ነበ​ሩት፤ በኵሩ ሰማያ፥ ሁለ​ተ​ኛው ዮዛ​ባት፥ ሦስ​ተ​ኛው ኢዮ​አስ፥ አራ​ተ​ኛው ሣካር፥ አም​ስ​ተ​ኛው ናት​ና​ኤል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እግዚአብሔርም ባርኮታልና ዖቤድኤዶም ልጆች ነበሩት፤ በኵሩ ሸማያ፥ ሁለተኛው ዮዛባት፥ ሦስተኛው ኢዮአስ፥ አራተኛው ሣካር፥ አምስተኛው ናትናኤል፥

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 26:4
11 Referencias Cruzadas  

ስለዚህም ታቦቱን ወደ ኢየሩሳሌም ላለመውሰድ ወሰነ፤ ይህንንም በማድረግ ፈንታ ከመንገድ መልሶ የጋት ከተማ ነዋሪ ወደ ሆነው ዖቤድኤዶም ተብሎ ወደሚጠራው ሰው ቤት አስገባው፤


እዚያም ሦስት ወር ተቀመጠ፤ እግዚአብሔርም ዖቤድኤዶምንና ቤተሰቡን ባረከ።


በቃል ኪዳኑ ታቦት ምክንያት እግዚአብሔር የዖቤድኤዶምን ቤተሰብና ያለውን ነገር ሁሉ እግዚአብሔር የባረከለት መሆኑን ንጉሥ ዳዊት ሰማ፤ ስለዚህም የቃል ኪዳኑን ታቦት በታላቅ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ሊወስደው በማሰብ ወደ ዖቤድኤዶም ቤት ሄዶ አወጣው።


ታቦቱም በዚያ ሦስት ወር ቈየ፤ እግዚአብሔርም የዖቤድኤዶምን ቤተሰብና የእርሱ የሆነውን ነገር ሁሉ ባረከ።


እነርሱንም እንዲረዱ የይዱቱን ልጅ ዖቤድኤዶምና ከእርሱ ጐሣ ሌሎች ሥልሳ ስምንት ሰዎች ተመደቡ፤ የይዱቱን ልጅ ዖቤድኤዶምና ሖሳ ለቅጽር በሮቹ ጥበቃ ኀላፊዎች ሆኑ።


አሳፍ መሪ፥ ዘካርያስም የእርሱ ረዳት ሆነው ተሾሙ፤ ይዒኤል፥ ሸሚራሞት፥ ይሒኤል፥ ማቲትያ፥ ኤሊአብ፥ በናያ፥ ዖቤድኤዶምና ይዒኤል መሰንቆና በገና ለመደርደር፥ አሳፍም ጸናጽል ለማንሿሿት ተመደቡ፤


ዔላም፥ የሆሐናንና ኤልየሆዔናይ ተብለው የሚጠሩት ናቸው።


ዓሚኤል፥ ይሳኮርና ፐዑልታይ ተብለው የሚጠሩት ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos