ንጉሡም ኢታይ ተብሎ የሚጠራውን የጌት ሰው እንዲህ አለው፤ “ከእኛ ጋር ለምን ትሄዳለህ? ተመልሰህ ከአዲሱ ንጉሥ ጋር ቈይ፤ አንተ ከአገርህ ወጥተህ በመጻተኛነት እዚህ የምትኖር የውጪ አገር ሰው ነህ፤
2 ሳሙኤል 6:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ታቦቱን ወደ ኢየሩሳሌም ላለመውሰድ ወሰነ፤ ይህንንም በማድረግ ፈንታ ከመንገድ መልሶ የጋት ከተማ ነዋሪ ወደ ሆነው ዖቤድኤዶም ተብሎ ወደሚጠራው ሰው ቤት አስገባው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዳዊት የእግዚአብሔር ታቦት ዐብሮት እንዲሆን ወደ ዳዊት ከተማ ይዞት ለመሄድ አልፈለገም፤ በዚህ ፈንታ አቅጣጫ ለውጦ የጋት ሰው ወደ ሆነው ወደ አቢዳራ ቤት ወሰደው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ዳዊት የጌታን ታቦት አብሮት እንዲሆን ወደ ዳዊት ከተማ ይዞት ለመሄድ አልፈለገም፤ በዚህ ፈንታ አቅጣጫ ለውጦ የጌት ሰው ወደ ሆነው ወደ ዖቤድ ኤዶም ቤት ወሰደው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም የእግዚአብሔርን ታቦተ ሕግ ወደ እርሱ ወደ ዳዊት ከተማ ያመጣት ዘንድ አልወደደም፤ ዳዊትም በጌት ሰው በአቢዳራ ቤት አገባት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ እርሱ ወደ ዳዊት ከተማ ያመጣው ዘንድ አልወደደም፥ ዳዊትም በጌት ሰው በአቢዳራ ቤት አገባው። |
ንጉሡም ኢታይ ተብሎ የሚጠራውን የጌት ሰው እንዲህ አለው፤ “ከእኛ ጋር ለምን ትሄዳለህ? ተመልሰህ ከአዲሱ ንጉሥ ጋር ቈይ፤ አንተ ከአገርህ ወጥተህ በመጻተኛነት እዚህ የምትኖር የውጪ አገር ሰው ነህ፤
ከዚህም በኋላ ሦስት ክፍል አድርጎ ላካቸው፤ ኢዮአብን የሢሶው፥ አቢሳይ የሢሶው፥ እንዲሁም የጋት ተወላጅ የሆነው ኢታይ የሢሶው አዛዦች ሆኑ፤ ንጉሡም ተከታዮቹን “እኔም ራሴ አብሬአችሁ እሄዳለሁ” አላቸው።
ዳዊት ምሽጉን ከያዘ በኋላ መኖሪያውን በዚያው ስፍራ አደረገ፤ እርስዋንም “የዳዊት ከተማ” ብሎ ጠራት፤ ከኮረብታው በስተ ምሥራቅ በኩል በዐፈር ከተደለደለው ስፍራ አንሥቶ በኮረብታው ዙሪያ ከተማይቱንም ሠራ።
አሳፍ መሪ፥ ዘካርያስም የእርሱ ረዳት ሆነው ተሾሙ፤ ይዒኤል፥ ሸሚራሞት፥ ይሒኤል፥ ማቲትያ፥ ኤሊአብ፥ በናያ፥ ዖቤድኤዶምና ይዒኤል መሰንቆና በገና ለመደርደር፥ አሳፍም ጸናጽል ለማንሿሿት ተመደቡ፤