2 ሳሙኤል 3:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኔርን ልጅ አበኔርን ታውቀዋለህ፤ እርሱ የመጣው አንተን አታሎ የምትወጣበትንና የምትገባበትን ለማየትና ምን እንደምታደርግ ለመሰለል ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኔርን ልጅ አበኔርን ታውቀዋለህ፤ የመጣው ሊያታልልህ፣ መውጣት መግባትህን ለማወቅና የምታደርገውን ሁሉ ሊሰልል ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኔርን ልጅ አበኔርን ታውቀዋለህ፤ የመጣው ሊያታልልህ፥ መውጫና መግቢያህን ሊያውቅብህና፥ የምታደርገውን ሁሉ ሊሰልልህ ነው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኔር ልጅ አበኔር ያታልልህ ዘንድ፥ መውጫህንና መግቢያህንም ያውቅ ዘንድ ፥ የምታደርገውንም ነገር ሁሉ ያስተውል ዘንድ እንደ መጣ አታውቅምን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኔር ልጅ አበኔር ያታልልህ ዘንድ፥ መውጫህንና መግቢያህንም ያውቅ ዘንድ፥ የምታደርገውንም ነገር ሁሉ ያስተውል ዘንድ እንደ መጣ አታውቅምን? አለው። |
ከእናንተ አንዱ ሄዶ ወንድማችሁን ያምጣ፤ የተናገራችሁት እውነት መሆኑ ተረጋግጦ ነጻ እስክትለቀቁ ድረስ የቀራችሁት እዚሁ በእስር ቤት ትቈያላችሁ አለበለዚያ ግን በፈርዖን ስም እምላለሁ፤ እናንተ ሰላዮች ናችሁ።”
ስለ እነርሱ ያየው ሕልም ሁሉ ትዝ አለውና “እናንተ ሰላዮች ናችሁ፤ የመጣችሁትም የአገራችንን ደካማነት እምን ላይ እንደ ሆነ ለመሰለል ነው” አላቸው።
የዐሞናውያን መሪዎች ንጉሡን እንዲህ አሉት፤ “ዳዊት እነዚህን ሰዎች የላከው አባትህን በማክበር የሐዘንህ ተካፋይ ለመሆን ይመስልሃልን? ከቶ እንዳይመስልህ! እርሱ እነዚህን መልእክተኞች የላካቸው በከተማይቱ ላይ አደጋ ለመጣል ያመች ዘንድ እንዲሰልሉለት አይደለምን?”
ስለዚህም ኢዮአብ ወደ ንጉሡ ቀርቦ እንዲህ አለው፦ “ይህ ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው? አበኔር ወደ አንተ መጥቶ ሳለ እንዲሁ እንዲሄድ ያሰናበትከው ስለምንድን ነው?
ኢዮአብ ከዳዊት ፊት ወጥቶ ከሄደ በኋላ አበኔርን ያመጡት ዘንድ መልእክተኞች ላከ፤ እነርሱም ከሲራ የውሃ ጒድጓድ አጠገብ መልሰው አመጡለት፤ ዳዊት ግን ስለዚህ ጉዳይ ምንም የሚያውቀው ነገር አልነበረም።
አበኔር ወደ ኬብሮን በደረሰ ጊዜ ኢዮአብ በግል ሊያነጋግረው የፈለገ በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ገለል አድርጎ ወሰደው፤ እዚያም ሆዱን ወግቶ ገደለው፤ ኢዮአብ ይህን ያደረገበት ምክንያት አበኔር ቀደም ብሎ ወንድሙን ዐሣሄልን ስለ ገደለበት ለመበቀል ነው።
ይህም ሁሉ የሚሆነው ንጉሠ ነገሥቱ የእናንተን አገር ወደምትመስል ምድር ወስዶ እስከሚያሰፍራችሁ ድረስ ነው፤ በዚያችም ምድር ወይን ጠጅ የሚገኝባቸው የወይን ተክል ቦታዎችና በቂ የእንጀራ እህል የሚመረትባቸው እርሻዎች አሉ፤ ምድሪቱም የወይራ ፍሬና የወይራ ዘይት እንዲሁም ማር. የሞላባት ናት፤ ንጉሠ ነገሥቱ የሚያዛችሁን ብትፈጽሙ በሕይወት ትኖራላችሁ እንጂ አትሞቱም፤ ስለዚህ ሕዝቅያስ ‘እግዚአብሔር ይታደጋችኋል’ እያለ በመስበክ አያሞኛችሁ፤
“እኔ ስለ አንተ ሁሉን ነገር ዐውቃለሁ፤ ምን እንደምታደርግና ወዴት እንደምትሄድ እመለከታለሁ፤ በእኔ ላይ በቊጣ መነሣሣትህንም ተረድቼአለሁ።
ሕዝቡም ስለ እርሱ በሹክሹክታ ይነጋገሩ ነበር፤ አንዳንዶቹ “እርሱ ደግ ሰው ነው” ሲሉ፥ ሌሎች ደግሞ “አይደለም፤ እርሱ ሕዝቡን ያስታል” ይሉ ነበር።
በሌላው ሰው ላይ የምትፈርድ አንተ ለራስህ የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው ሰው ላይ ስትፈርድ በራስህ ላይ ትፈርዳለህ፤ አንተ በሰው ላይ እየፈረድክ፥ ያ የፈረድክበት ሰው የሚያደርገውን ታደርጋለህ።