2 ሳሙኤል 3:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አበኔር ኻያ ሰዎችን አስከትሎ ዳዊት ወዳለበት ወደ ኬብሮን በመጣ ጊዜ ዳዊት ግብዣ አደረገላቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አበኔር ከሃያ ሰዎች ጋራ ዳዊት ወዳለበት ወደ ኬብሮን መጣ፤ ዳዊትም ለአበኔርና ዐብረውት ለነበሩት ሰዎች ግብዣ አደረገላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አበኔር ከሃያ ሰዎች ጋር ዳዊት ወዳለበት ወደ ኬብሮን በመጣ ጊዜ፤ ዳዊት ለአበኔርና አብረውት ለነበሩት ሰዎች ግብዣ አደረገላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አበኔርም ከሃያ ሰዎች ጋር ወደ ዳዊት ወደ ኬብሮን መጣ፤ ዳዊትም ለአበኔርና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሰዎች ግብዣ አደረገላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አበኔርም ከሀያ ሰዎች ጋር ወደ ዳዊት ወደ ኬብሮን መጣ። ዳዊትም ለአበኔርና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሰዎች ግብዣ አደረገላቸው። |
አበኔር ለብንያም ነገድ ሕዝብም ይህንኑ ተናገረ፤ ከዚያም በኋላ የብንያምና የእስራኤል ሕዝብ ለማድረግ የተስማሙበትን ጉዳይ ለዳዊት ለመንገር ወደ ኬብሮን ሄደ።
አበኔርም ዳዊትን “ከአንተ ጋር እንዲነጋገሩና እንዲዋዋሉ አንተም ልብህ በተመኘው ሁሉ ላይ እንድትነግሥ ለማድረግ ወደ እስራኤላውያን ልሂድ” አለው። በዚህም ዐይነት ዳዊት አበኔርን በሰላም አሰናበተው።
አርጤክስስ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ባለሟሎቹ ለሆኑት ባለሥልጣኖችና አስተዳዳሪዎች ሁሉ ታላቅ ግብዣ አደረገ፤ በግብዣውም ላይ የፋርስና የሜዶን ጦር አዛዦች፥ አገረ ገዢዎችና የክፍላተ ሀገር አስተዳዳሪዎች ተገኝተው ነበር።
አቢጌልም እንደ ቤተ መንግሥት ግብር ታላቅ ግብዣ በማድረግ ላይ ወደነበረው ወደ ናባል ተመልሳ ሄደች፤ እርሱም ሰክሮ በደስታ ይፈነድቅ ስለ ነበር እስከ ማግስቱ ጧት ድረስ ምንም ቃል አልነገረችውም፤