2 ሳሙኤል 22:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእግዚአብሔር በቀር ማን ነው አምላክ? ከእርሱስ በቀር መጠጊያ የሚሆን ማነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእግዚአብሔር በቀር ማን አምላክ አለ? ከአምላካችንስ በቀር ዐለት ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጌታ በቀር አምላክ ማን ነው፤ ከአምላካችንስ በቀር ዓለት ማን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእግዚአብሔር በቀር ጽኑዕ ማን ነው? ከአምላካችንስ በቀር ፈጣሪ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን ነው? ከአምላካችንስ በቀር አምባ ማን ነው? |
የሠራዊት አምላክ፥ የእስራኤል ንጉሥና አዳኝ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የመጀመሪያውም የመጨረሻውም እኔ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም።
እናንተ አትፍሩ፤ አትደንግጡ፤ ከጥንት ዘመናት ጀምሮ አስቀድሜ አልነገርኳችሁምን? ወይስ አልገለጽኩላችሁምን? ለዚህም እናንተ ምስክሮቼ ናቸሁ፤ ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? ከእኔ ሌላ መጠጊያ አለት የለም፤ ማንም የለም።”
ጉዳይህን አቅርበህ ገለጻ አድርግ፤ ከብዙ ጊዜ በፊት ይህን የተናገሩ ተሰብስበው ይመካከሩ፤ በጥንት ጊዜ የተናገረው ማነው? እኔ እግዚአብሔር አልነበርኩምን? ከእኔ በቀር ጻድቅና አዳኝ አምላክ የለም።
የያዕቆብ አምላክ ግን እንደ እነርሱ አይደለም፤ እርሱ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው። እስራኤልንም የራሱ ሕዝብ እንዲሆን መርጦታል፤ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
“አምላክ እኔ ብቻ መሆኔን ዕወቁ፤ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ የምገድልም፥ ሕይወትንም የምሰጥ እኔ ነኝ፤ አቈስላለሁ፤ እፈውሳለሁም ከእጄ ማንም ሊያድን አይችልም