2 ሳሙኤል 22:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔርን ሕጎች ሁሉ እፈጽማለሁ፤ ሥርዓቱንም ከማክበር ወደ ኋላ አላልኩም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕጎቹ ሁሉ በፊቴ ናቸው፤ ከሥርዐቱም ዘወር አላልሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕጎቹ ሁሉ በፊቴ ናቸው፤ ከሥርዓቱም አልራቅሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነበርና፤ ጽድቁም ከእኔ አልራቀምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነበረና፥ ከሥርዓቱም አልራቅሁምና። |
ራሱንም ከወገኖቹ ከእስራኤላውያን እበልጣለሁ ብሎ እንዳይታበይና ከእግዚአብሔርም ትእዛዞች እንዳይርቅ ይጠብቀዋል። ይህን ቢያደርግ ለብዙ ዘመን ይነግሣል፤ ልጆቹም በእስራኤል ላይ ለብዙ ዘመን ይነግሣሉ።
“እነዚህን ትእዛዞች ብታዳምጥና በታማኝነትም ብትፈጽማቸው፥ እግዚአብሔር አምላክህ ለቀድሞ አባቶችህ በመሐላ የሰጠውን ቃል ኪዳንና ዘለዓለማዊ ፍቅር ለአንተም ያጸናልሃል፤