La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 22:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በጣም በርትተውብኝ ከነበሩት ከኀይለኞች ጠላቶቼና ከሚጠሉኝ ሰዎች ሁሉ እጅ እግዚአብሔር አዳነኝ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከብርቱ ጠላቶቼ አዳነኝ፤ ከሚበረቱብኝ ባላጋሮቼም ታደገኝ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በርትተውብኝ ነበርና፥ ከብርቱ ጠላቶቼ፥ ከሚጠሉኝም ታደገኝ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከብ​ር​ቱ​ዎች ጠላ​ቶቼ፥ ከሚ​ጠ​ሉ​ኝም አዳ​ነኝ፤ በር​ት​ተ​ው​ብኝ ነበ​ርና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከብርቱዎች ጠላቶቼ፥ ከሚጠሉኝም አዳነኝ፥ በርትተውብኝ ነበርና።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 22:18
8 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ዳዊትን ከሳኦልና ከሌሎቹም ጠላቶቹ እጅ በመታደግ ባዳነው ጊዜ ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር ክብር ዘመረ፦


እግዚአብሔር ከላይ ሆኖ እጁን በመዘርጋት ያዘኝ፤ ከጥልቅ ውሃም ስቦ አወጣኝ።


እኔ በተቸገርኩበት ጊዜ በጠላትነት ተነሡብኝ በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ጠበቀኝ።


ጌታ ሆይ! ተነሥ! አምላኬ ሆይ! መጥተህ አድነኝ! የጠላቶቼን መንጋጋ ስበር፤ ጥርሶቻቸውንም አድቅቅ።


ጌታ ሆይ! ሁለመናዬ እንዲህ ብሎ ይናገራል፤ ተበዳዮችን ከበደለኛ የሚያድን፥ ድኾችንና ተጨቋኞችን ከነጣቂዎች የሚጠብቅ እንደ አንተ ያለ ማነው?


እኔ ወደ አንተ በምጣራበት ቀን፥ ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር መሆኑንም በዚህ ዐውቃለሁ።


ስለዚህ እርሱ ለሞት ከሚያደርስ አደጋ አድኖናል፤ ያድነናልም፤ ደግሞም እንደሚያድነን ተስፋችን በእርሱ ነው።


ነገር ግን መልእክቱ በእኔ አማካይነት በሙሉ እንዲነገርና አሕዛብ ሁሉ እንዲሰሙት ጌታ ከእኔ ጋር ሆኖ አበረታኝ፤ ከአንበሳም አፍ ድኛለሁ።