ከዚህ በኋላ የይሁዳ ሰዎች ወደ ኬብሮን መጡ፤ ዳዊትንም ቀብተው የይሁዳ ንጉሥ አደረጉት። ዳዊት ገለዓዳውያን የሆኑ የያቤሽ ሰዎች ሳኦልን እንደ ቀበሩት በሰማ ጊዜ፥
2 ሳሙኤል 21:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት፥ የሳኦል ቁባት የነበረችው ሪጽፋ ያደረገችውን በሰማ ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሳኦል ቁባት የኢዮሄል ልጅ ሪጽፋ ያደረገችውን ዳዊት በሰማ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሳኦል ዕቁባት የአያ ልጅ ሪጽፋ ያደረገችውን ዳዊት በሰማ ጊዜ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሳኦልም ዕቅብት የኢዮሔል ልጅ ሩጻፋ ያደረገችውን ለዳዊት ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሳኦልም ቁባት የኢዮሄል ልጅ ሪጽፋ ያደረገችውን ለዳዊት ነገሩት። |
ከዚህ በኋላ የይሁዳ ሰዎች ወደ ኬብሮን መጡ፤ ዳዊትንም ቀብተው የይሁዳ ንጉሥ አደረጉት። ዳዊት ገለዓዳውያን የሆኑ የያቤሽ ሰዎች ሳኦልን እንደ ቀበሩት በሰማ ጊዜ፥
ከዚህ በኋላ የሳኦል ቊባት የነበረችው የአያ ልጅ ሪጽፋ ሬሳዎቹ ባሉበት ስፍራ አጠገብ በሚገኘው ቋጥኝ ድንጋይ ላይ ማቅ ዘርግታ ከስሩ ተቀመጠች፤ እርስዋም ከመከር ጊዜ መጀመሪያ አንሥቶ ዝናብ እስከሚጥልበት ጊዜ ድረስ እዚያ ቈየች፤ ቀን ቀን ወፎች በሬሳዎቹ ላይ እንዳያርፉ እየተከላከለች፥ ሌሊት ሌሊትም አውሬ እንዳይበላቸው ትጠብቃቸው ነበር።
በገለዓድ ምድር ወደምትገኘው ወደ ያቤሽ ሕዝብ ሄዶ የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን ዐፅም አመጣ፤ የያቤሽ ሕዝብ ዐፅሙን ያገኙት ፍልስጥኤማውያን ሳኦልን በጊልቦዓ በገደሉበት ቀን ሬሳዎችን ከሰቀሉበት ከቤትሻን አደባባይ በመስረቅ ነበር።