ኢዮአብ በሌላው እጁ የያዘውን ሰይፍ ስላላየ ዐማሣ አልተጠነቀቀም ነበርና ኢዮአብ በሆዱ ሻጠበት፤ የሆድ ዕቃውም መሬት ላይ ተዘረገፈ፤ ወዲያውኑ ስለ ሞተም ኢዮአብ በድጋሚ አልወጋውም። ከዚህ በኋላ ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳ የቢክሪን ልጅ ሼባዕን ማሳደዳቸውን ቀጠሉ።
2 ሳሙኤል 20:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአብም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ ከተማችሁን አልደመስስም! ከቶም አላፈርስም! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአብም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ይህስ ከእኔ ይራቅ! መዋጡና ማጥፋቱ አሁንም ከእኔ ይራቅ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአብም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ይህስ ከእኔ ይራቅ! መዋጡና ማጥፋቱ አሁንም ከእኔ ይራቅ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብም መልሶ፥ “ይህ ማፍረስና ማጥፋት ከእኔ ይራቅ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም መልሶ፦ ይህ መዋጥና ማጥፋት ከእኔ ይራቅ፥ |
ኢዮአብ በሌላው እጁ የያዘውን ሰይፍ ስላላየ ዐማሣ አልተጠነቀቀም ነበርና ኢዮአብ በሆዱ ሻጠበት፤ የሆድ ዕቃውም መሬት ላይ ተዘረገፈ፤ ወዲያውኑ ስለ ሞተም ኢዮአብ በድጋሚ አልወጋውም። ከዚህ በኋላ ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳ የቢክሪን ልጅ ሼባዕን ማሳደዳቸውን ቀጠሉ።
የእኔ ከተማ ግን ታላቅ ከተማ ናት፤ በእስራኤል ሰላም የሰፈነባትና ታማኝ ከተማ እርስዋ ናት፤ ታዲያ፥ አንተ ይህችን ከተማ ለመደምሰስ ለምን ታቅዳለህ? የእግዚአብሔር ርስት የሆነውን ነገር ለማፍረስ ትፈልጋለህን?”
የእኛ ዕቅድ ይህ አይደለም፤ የተራራማው የኤፍሬም አገር ተወላጅ የሆነ ሼባዕ ተብሎ የሚጠራ የቢክሪ ልጅ በንጉሥ ዳዊት ላይ ዐመፅ አስነሥቶአል፤ ብቻ ይህ ሰው ይሰጠኝ እንጂ እኔ ከተማይቱን ለቅቄ እሄዳለሁ።” እርስዋም “ራሱን ቈርጠን በግንብ ላይ እንወረውርልሃለን” አለችው።
“እግዚአብሔር ሆይ! ይህን ውሃ ከቶ ልጠጣው አልችልም! እኔ እርሱን ብጠጣ፥ በነፍሳቸው ቈርጠው የሄዱትን የእነዚህን ኀያላን ሰዎች ደም እንደ ጠጣሁ ይቈጠራል!” አለ፤ ውሃውንም መጠጣት እምቢ አለ። ዝነኞች የሆኑት ሦስቱ ኀያላን ወታደሮች የፈጸሙአቸው የጀግንነት ተግባሮች እነዚህ ናቸው።