La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 20:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢዮአብ ወደዚያ በሄደ ጊዜም ሴትዮዋ “ኢዮአብ የምትባለው አንተ ነህን?” ስትል ጠየቀችው። እርሱም “አዎ እኔ ነኝ” አላት። እርስዋም “ጌታዬ፥ እስቲ አድምጠኝ” አለችው፤ እርሱም “እነሆ፥ አዳምጥሻለሁ” አላት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢዮአብ ወደ እርሷ ሄደ፤ እርሷም፣ “ኢዮአብ አንተ ነህ?” ስትል ጠየቀችው። እርሱም፣ “አዎን እኔ ነኝ” ብሎ መለሰላት። እርሷም፣ “እንግዲህ አገልጋይህ የምትለውን ስማ” አለችው። እርሱም፣ “ዕሺ፣ አደምጣለሁ” አላት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢዮአብ ወደ እርሷ ቀረበ፤ እርሷም፥ “ኢዮአብ አንተ ነህ?” ስትል ጠየቀችው። እርሱም፥ “አዎን እኔ ነኝ” ብሎ መለሰላት። እርሷም፥ “እንግዲህ አገልጋይህ የምትለውን አድምጥ” አለችው። እርሱም፥ “እያዳመጥኩ ነው” አላት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሴቲ​ቱም፥ “ኢዮ​አብ አንተ ነህን?” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “እኔ ነኝ” ብሎ መለ​ሰ​ላት። እር​ስ​ዋም፥ “የባ​ሪ​ያ​ህን ቃል ስማ” አለ​ችው። ኢዮ​አ​ብም፥ “እሰ​ማ​ለሁ” አላት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ እርስዋም ቀረበ፥ ሴቲቱም፦ ኢዮአብ አንተ ነህን? አለች። እርሱም፦ እኔ ነኝ ብሎ መለሰላት። እርስዋም፦ የባሪያህን ቃል ስማ አለችው። እርሱም፦ እሰማለሁ አላት።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 20:17
4 Referencias Cruzadas  

ሴቲቱም “ንጉሥ ሆይ! እንደገናም እኔ አገልጋይህ አንድ ነገር እንድናገር ፍቀድልኝ” አለችው። እርሱም “እሺ ተናገሪ” አላት።


በከተማይቱ ውስጥ የምትኖር አንዲት ብልኅ ሴት በቅጽሩ ላይ ሆና ድምፅዋን ከፍ በማድረግ “ስሙ! ስሙ! ኢዮአብ ወደዚህ ይመጣ ዘንድ ንገሩት፤ እኔ ላነጋግረው እፈልጋለሁ!” አለች።


እርስዋም እንዲህ አለችው፤ “በድሮ ዘመን ‘ወደ አቤል ከተማ ሄዳችሁ የጥያቄአችሁን መልስ ከዚያ ታገኛላችሁ’ ይባል ነበር፤ ሰዎችም የሚያደርጉት ይህንኑ ነበር።


በጫማውም ላይ ወድቃ እንዲህ አለች፦ “ጌታዬ ሆይ! እባክህ የእኔን የአገልጋይህን ቃል አድምጠኝ! በደሉን እኔ ልሸከም፤