“ሳኦልና ዮናታን በአስደናቂ ፍቅር ኖሩ፤ በሕይወትም ሆነ በሞት ላለመለያየት ተባበሩ፤ እነርሱም ከንስር የፈጠኑ፥ ከአንበሳም የበረቱ ነበሩ።
2 ሳሙኤል 2:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአብ፥ አቢሳ፥ ዐሣሄል ተብለው የሚጠሩት ሦስቱም የጸሩያ ልጆች እዚያ ነበሩ፤ በሩጫ እንደ በረሓ ሚዳቋ ፈጣን የነበረው አሳሔል፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሦስቱ የጽሩያ ወንዶች ልጆች ኢዮአብ፣ አቢሳና አሣሄል እዚያው ነበሩ። አሣሄል እንደ ዱር ሚዳቋ በሩጫ ፈጣን ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሦስቱ የጽሩያ ልጆች ኢዮአብ፥ አቢሳና አሣሄል እዚያው ነበሩ። አሣሄል እንደ ዱር ሚዳቋ በሩጫ ፈጣን ነበረ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ሦስቱ የሦርህያ ልጆች ኢዮአብና አቢሳ፥ አሣሄልም ነበሩ፤ የአሣሄልም እግሮቹ ፈጣኖች ነበሩ፤ እንደ ዱር ሚዳቋም ሯጭ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ሦስቱ የጽሩያ ልጆች ኢዮአብና አቢሳ አሣሄልም ነበሩ፥ አሣሄልም እንደ ዱር ሚዳቋ በሩጫ ፈጣን ነበረ። |
“ሳኦልና ዮናታን በአስደናቂ ፍቅር ኖሩ፤ በሕይወትም ሆነ በሞት ላለመለያየት ተባበሩ፤ እነርሱም ከንስር የፈጠኑ፥ ከአንበሳም የበረቱ ነበሩ።
ከሠላሳዎቹ መካከል የሌሎቹ ሰዎች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ የኢዮአብ ወንድም ዐሣሄል፤ የቤተልሔሙ ተወላጅ የዶዶ ልጅ ኤልሐናን፤ የሐሮድ ተወላጆች የሆኑት ሻማና ኤሊቃ፤ የፌሌጥ ተወላጅ የሆነው ሔሌጽ፤ የተቆዓ ተወላጅ የሆነው የዒቄሽ ልጅ ዒራ፤ የዐናቶት ተወላጅ የሆነው አቢዔዜር፤ የሑሻ ተወላጅ የሆነው መቡናይ፤ የአሖሕ ተወላጅ የሆነው ጻልሞን፤ የነጦፋ ተወላጅ የሆነው ማህራይ፤ የነጦፋ ተወላጅ የሆነው የባዕና ልጅ ሔሌብ፤ በብንያም ግዛት የምትገኘው የጊብዓ ተወላጅ የሆነው የሪባይ ልጅ ኢታይ፤ የፒርዓቶን ተወላጅ የሆነው በናያ፤ በጋዓሽ ሸለቆ አጠገብ የተወለደው ሂዳይ፤ የዓርባ ተወላጅ የሆነው ኢቢዓልቦን፤ የባርሑም ተወላጅ የሆነው ዓዝማዌት፤ የሻዓልቦን ተወላጅ የሆነው ኤልያሕባ፤ የያሼን ልጆች፤ ዮናትን፤ የሐራር ተወላጅ የሆነው ሻማ፤ የሐራር ተወላጅ የሆነው የሻራር ልጅ አሒአም፤ የማዕካ ተወላጅ የሆነው የአሐሰባይ ልጅ ኤሊፌሌጥ፤ የጊሎ ተወላጅ የሆነው የአኪጦፌል ልጅ ኤሊዓም፤ የቀርሜሎስ ተወላጅ የሆነው ሔጽሮ፤ የዐረብ ተወላጅ የሆነው ፓዓራይ፤ የጾባ ልጅ የሆነው የናታን ልጅ ዪግአል የጋድ ተወላጅ የሆነው ባኒ፤ የዐሞን ተወላጅ የሆነው ጼሌቅ፤ የኢዮአብ ጋሻ ጃግሬ የነበረውና የበኤሮት ተወላጅ የሆነው ናሕራይ፤ የያቲር ተወላጆች የሆኑት ዒራና ጋሬብ፤ ሒታዊው ኦርዮን። ዝነኞች የሆኑት ኀያላን ወታደሮች ጠቅላላ ድምር ሠላሳ ሰባት ነበር።
“የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የእስራኤል ሕዝብ የጦር መሪዎች ከነበሩት በኔር ልጅ አበኔርና በይቴር ልጅ ዐማሣ ላይ ያደረገውን ታስታውሳለህ፤ ሁለት በጦርነት ጊዜ ላፈሰሱት ደም በቀል በሰላም ጊዜ እነርሱን ገድሎ የወገቡን ድግና የእግሩን ጫማ በደም በክሎ በእኔ ላይ ምን እንዳደረገ ታውቃለህ።
ከሠላሳዎቹ መካከል የሌሎቹ ሰዎች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ የኢዮአብ ወንድም ዐሣሄል፥ የቤተልሔሙ ተወላጅ የዶዶ ልጅ ኤልሐናን፥ የሐሮድ ተወላጅ ሻሞት፥ የፌሌጥ ተወላጅ የሆነው ሔሌጽ፥ የተቆዓ ተወላጅ የሆነው የዒቄሽ ልጅ ዒራ፥ የዐናቶት ተወላጅ የሆነው አቢዔዜር፥ የሑሻ ተወላጅ የሆነው ሲበካይ፥ የአሖሕ ተወላጅ የሆነው ዒላይ፥ የነጦፋ ተወላጅ የሆነው ማህራይ፥ የነጦፋ ተወላጅ የሆነው የባዕና ልጅ ሔሌድ፥ በብንያም ግዛት የምትገኘው የጊብዓ ተወላጅ የሪባይ ልጅ ኢታይ፥ የፒርዓቶን ተወላጅ የሆነው በናያ፥ በጋዓሽ አጠገብ ባሉት ሸለቆዎች የተወለደው ሑራይ፥ የዓረባ ተወላጅ የሆነው አቢኤል፥ የባሕሩም ተወላጅ የሆነው ዓዝማዌት፥ የሻዓልቦን ተወላጅ የሆነው ኤልያሕባ፥ የጊዞን ተወላጅ የሆነው ሃሼም፥ የሃራር ተወላጅ የሆነው የሻጌ ልጅ ዮናታን፥ የሀራር ተወላጁ የሳካር ልጅ አሒአም፥ የኡር ልጅ ኤሊፋል፥ የመኬራ ተወላጅ የሆነው ሔፌር፥ የፐሎን ተወላጅ የሆነው አሒያ፥ የቀርሜሎስ ተወላጅ የሆነው ሔጽሮ፥ የኤዝባይ ልጅ ናዕራይ፥ የናታን ወንድም ዮኤል፥ የሃግሪ ልጅ ሚብሐር፥ የዐሞን ተወላጅ የሆነው ጼሌቅ፥ የበኤሮት ተወላጅና የኢዮአብ ጋሻጃግሬ የነበረው ናሕራይ፥ የያቲር ተወላጆች የሆኑት ዒራና ጋሬብ፥ ሒታዊው ኦርዮን፥ የአሕላይ ልጅ ዛባድ፥ የሺዛ ልጅ ዐዲና፤ (ይህ ሰው የራሱ ቡድን የሆኑ ሠላሳ ወታደሮችን እንደ ያዘ ከሮቤል ነገድ የታወቀ ነበር፤) የማዕካ ልጅ ሐናን፥ የሚታን ተወላጅ የሆነው ኢዮሣፍጥ፥ የዐሽተራ ተወላጅ የሆነው ዑዚያ፥ የዓሮዔር ተወላጅ የሆነው የሆታም ልጆች ሻማዕና ይዒኤል፥ የቲጺ ተወላጅ የሆነው የሺምሪ ልጆች ይዲዕኤልና ዮሐ፥ የማሐዋ ተወላጅ የሆነው ኤሊኤል፥ የኤልናዓም ልጆች ይሪባይና ዮሻውያ፥ የሞአብ ተወላጅ የሆነው ዩትማ፥ የጾባ ተወላጆች የሆኑት ኤሊኤል፥ ዖቤድና ያዕሲኤል።
ዳዊት በበረሓ በሚገኘው ምሽግ ውስጥ ሳለ ከጋድ ነገድ መጥተው ከእርሱ ሠራዊት ጋር የተባበሩት ዝነኞችና የጦር ልምድ ያላቸው ወታደሮች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፤ እነርሱ ጋሻና ጦር ይዘው በመዋጋት የታወቁ ነበሩ፤ አስፈሪነታቸው እንደ አንበሳ ሲሆን ፈጣንነታቸው በተራራ ላይ እንደሚዘል ሚዳቋ ነበር፤
የእነርሱም ስም በሚከተለው ሁኔታ በየማዕርጋቸው በቅደም ተከተል ተራ ተዘርዝሮአል፦ ዔዜር፥ አብድዩ ኤሊአብ፥ ሚሽማና፥ ኤርምያስ፥ ዓታይ፥ ኤሊኤል፥ ዮሐናን፥ ኤልዛባድ፥ ኤርምያስ ማክባናይ።
በዚህ ዓለም የተመለከትኩት ሌላም ነገር አለ፤ ይኸውም ፈጣን ሯጮች በአሸናፊነት አይወጡም፤ ጀግኖችም በጦርነት ድል አያደርጉም፤ ጠቢባን የዕለት እንጀራን፥ ብልኆች ሀብትን አያገኙም፤ ችሎታ ያላቸውም ሰዎች በማዕርግ አያድጉም፤ ነገር ግን ሁሉንም ጊዜና ዕድል ያጋጥማቸዋል፤
የሌሊቱ ጨለማ እስከሚወገድ፤ የማለዳው ነፋስ እስከሚነፍስ፤ ውዴ ሆይ! እንደ ዋልያ ወይም እንደ አጋዘን ግልገል በገደላማ ተራራዎች ላይ እየሮጥክ ተመለስ።
ከዚህም በኋላ ዳዊት ሒታዊውን አቤሜሌክንና ከጸሩያ ልጆች የኢዮአብን ወንድም አቢሳን “ከእናንተ ከሁለታችሁ ከእኔ ጋር አብሮ ወደ ሳኦል ሰፈር የሚሄድ ማን ነው?” ሲል ጠየቃቸው። አቢሻይም “እኔ እሄዳለሁ” ሲል መለሰ።