La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 19:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንተ የሚወዱህን ትጠላለህ፤ የሚጠሉህን ግን ትወዳለህ! ስለ ጦር መኰንኖችህና ስለ ወታደሮችህ ሁሉ ምንም የማይገድህ መሆኑን በግልጥ አሳይተሃል፤ አቤሴሎም በሕይወት ቢኖርና እኛ ሁላችን ብንጠፋ ኖሮ እጅግ እንደምትደሰት ተገንዝቤአለሁ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሚጠሉህን ትወድዳለህ፤ የሚወድዱህን ትጠላለህ፤ የጦር አዛዦችህና ወታደሮቻቸው ለአንተ ምንህም እንዳይደሉ ይኸው ዛሬ ግልጽ አድርገሃል፤ ዛሬ አቤሴሎም በሕይወት ኖሮ እኛ ሁላችን ዐልቀን ቢሆን ደስ እንደሚልህ በዛሬው ዕለት ለማየት በቅቻለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም ኢዮአብ ወደ ንጉሡ ቤት ገብቶ እንዲህ አለው፤ “የአንተን፥ የወንዶችንና የሴቶች ልጆችህን፥ የሚስቶችህንና የዕቁባቶችህን ሕይወት ያተረፉትን ሰዎች ሁሉ ዛሬ አሳፍረሃቸዋል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አንተ የሚ​ጠ​ሉ​ህን ትወ​ድ​ዳ​ለህ፤ የሚ​ወ​ድ​ዱ​ህ​ንም ትጠ​ላ​ለህ፤ አለ​ቆ​ች​ህና አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እን​ደ​ማ​ይ​ጠ​ቅ​ሙህ እን​ደ​ም​ታ​ስብ ዛሬ ገል​ጠ​ሃ​ልና፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም ድኖ ቢሆን ዛሬ እኛ ሁላ​ችን እን​ሞት እንደ ነበር አው​ቃ​ለሁ። ይህ በፊ​ትህ ላንተ ቀና ነበ​ረና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አንተ የሚጠሉህን ትወድዳለህ፦ የሚወድዱህንም ትጠላለህ። መሳፍንትህና ባሪያዎችህን እንዳታስብ ዛሬ ገልጠሃል፥ ዛሬ ሁላችን ሞተን ቢሆን ኖር አቤሴሎምም ድኖ ቢሆን ኖሮ ደስ ያሰኘህ እንደ ነበረ ዛሬ አያለሁ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 19:6
6 Referencias Cruzadas  

በዚህ ጊዜ ኢዮአብ ወደ ንጉሡ ቤት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “የአንተን የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን፥ የሚስቶችህንና የቊባቶችህን ሕይወት ያዳኑትን ሰዎች ዛሬ አሳፍረሃቸዋል፤


ይልቅስ አሁን ተነሥና ወታደሮችህን አበረታታ፤ ይህንን ባታደርግ ግን ነገ ጠዋት ከእነርሱ አንዱ እንኳ ከአንተ ጋር እንደማይሆን በእግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ፤ ይህም በሕይወትህ ከደረሰብህ መከራ ሁሉ እጅግ የከፋ ይሆንብሃል።”


ንጉሡን የማትጠቅም ነህ፤ መኳንንቱንም ክፉዎች ናችሁ፤ የሚላቸው ማነው?


ጳውሎስም “ወንድሞቼ ሆይ! የካህናት አለቃ መሆኑን አላወቅሁም ነበር፤ ምክንያቱም ‘በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ ቃል አትናገር’ የሚል ተጽፎአል” አለ።