እኔ ባሪያህ ይህን ያኽል ቸርነትና ታማኝነት ልታሳየኝ የሚገባኝ አልነበርኩም፤ ዮርዳኖስን ተሻግሬ ስመጣ ከምመረኰዘው በትር በቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን እነዚህን በሁለት ቡድን የተከፈሉ ወገኖች ይዤ ተመልሻለሁ።
2 ሳሙኤል 19:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሆይ! የአባቴ ቤተሰብ ሁሉ በሞት መቀጣት የሚገባው ነበር፤ ንጉሥ ሆይ! አንተ ግን በገበታህ ቀርቤ እንድመገብ መብት ሰጠኸኝ፤ ከዚህ የበለጠም ቸርነት እንዲደረግልኝ መጠየቅ አይገባኝም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአባቴ ቤት ሁሉ ከንጉሥ ጌታዬ ሞት እንጂ ሌላ የሚገባው አልነበረም፤ አንተ ግን ባሪያህን በማእድህ ከሚካፈሉት ጋራ አስቀመጥኸው፤ ከዚህ በላይ ይደረግልኝ ብዬ ንጉሡን ለመጠየቅ ምን መብት አለኝ?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታዬ በንጉሡ ፊትም የእኔን የአገልጋይህን ስም አጥፍቶአል፤ ንጉሥ ጌታዬ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለሆንህ ደስ ያሰኘህን አድርግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአባቴ ቤት ሁሉ በጌታዬ በንጉሥ ዘንድ ሞት የሚገባቸው ነበሩ፤ አንተ ግን እኔን ባሪያህን በገበታህ በሚበሉ መካከል አስቀመጥኸኝ፤ ለንጉሥ ደግሞ ለመናገር ምን መብት አለኝ?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአባቴ ቤት ሁሉ በጌታዬ በንጉሡ ዘንድ ሞት የሚገባቸው ነበሩ፥ አንተ ግን እኔን ባሪያህን በገበታህ በሚበሉ መካከል አስቀመጥኸኝ፥ ለንጉሥ ደግሞ ለመናገር ምን መብት አለኝ? |
እኔ ባሪያህ ይህን ያኽል ቸርነትና ታማኝነት ልታሳየኝ የሚገባኝ አልነበርኩም፤ ዮርዳኖስን ተሻግሬ ስመጣ ከምመረኰዘው በትር በቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን እነዚህን በሁለት ቡድን የተከፈሉ ወገኖች ይዤ ተመልሻለሁ።
እንዲሁም ንጉሥ ሆይ! ንጉሥ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለ ሆነና መልካሙን ከክፉው ለይቶ ስለሚያውቅ የተስፋ ቃልህ በሰላም እንድኖር ይረዳኛል ብዬ አስቤ ነው እንግዲህ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን!”
እርሱም ይህን ያደረገው ነገሮችን ሁሉ ለማስተካከል በማሰብ ነው፤ ንጉሥ ሆይ! አንተ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ጥበበኛ ነህ፤ የሚሆነውንም ነገር ሁሉ ታውቃለህ።”
ንጉሡም “የጌታህ የሳኦል የልጅ ልጅ መፊቦሼት የት ነው?” ሲል ጠየቀው። ጺባም “እስራኤላውያን የአያቱን የሳኦልን መንግሥት መልሰው እንደሚሰጡት ስለ ተማመነ እርሱ አሁን የሚገኘው በኢየሩሳሌም ነው” ሲል መለሰ።
አንተ፥ ወንዶች ልጆችህና አገልጋዮችህ ለጌታህ ለሳኦል ቤተሰብ ምድሪቱን አርሳችሁ ምግብ ይሆናቸው ዘንድ መከሩን አገቡላቸው፤ የጌታህ የልጅ ልጅ መፊቦሼት ግን ዘወትር በገበታዬ የሚቀርብ ተመጋቢ ይሆናል፤” ጺባ ዐሥራ አምስት ወንዶች ልጆችና ኻያ አገልጋዮች ነበሩት።
ይህ የሠራኸው ሥራ ልክ አይደለም፤ አበኔር፥ እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፥ እግዚአብሔር ቀብቶ ያነገሠውን ጌታችሁን ንጉሡን መጠበቅ ስላልቻላችሁ ሁላችሁም ሞት ይገባችኋል! በራስጌው የነበረው የንጉሡ ጦርና እንዲሁም የውሃ መቅጃው አሁን የት እንዳለ እስቲ ተመልከት!” አለው።