2 ሳሙኤል 19:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእርሱም ጋር የብንያም ነገድ የሆኑ አንድ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤ የሳኦል ቤተሰብ አገልጋይ የነበረው ጺባም ከዐሥራ አምስት ወንዶች ልጆቹና ከኻያ አገልጋዮቹ ጋር መጣ፤ ወደ ዮርዳኖስም ወንዝ እየተጣደፉ ደርሰው በንጉሡ ፊት ቀረቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱም ጋራ አንድ ሺሕ ብንያማውያን፣ እንዲሁም የሳኦል ቤተ ሰብ አገልጋይ ሲባ ከዐሥራ ዐምስት ወንዶች ልጆቹና ከሃያ አሽከሮቹ ጋራ ሆኖ ዐብረውት ነበሩ። ከዚያም ንጉሡ ወዳለበት ወደ ዮርዳኖስ በጥድፊያ ወረዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የባሑሪም ሰው የሆነው የጌራ ልጅ ብንያማዊው ሺምዒ ከይሁዳ ሰዎች ጋር ሆኖ ንጉሥ ዳዊትን ለመቀበል ፈጥኖ ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም ጋራ ከብንያም ወገን የሆኑ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤ የሳኦልም ቤት አገልጋይ ሲባ ከእርሱም ጋር ዐሥራ አምስቱ ልጆቹና ሃያው አገልጋዮቹ ነበሩ፤ በንጉሡም ፊት በቀጥታ ወደ ዮርዳኖስ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም ጋር ብንያማውያን የሆኑ ሺህ ሰዎች ነበሩ፥ የሳኦልም ቤት ባሪያ ሲባ ከእርሱም ጋር አሥራ አምስቱ ልጆችና ሀያው ባሪያዎች ነበሩ፥ በንጉሡም ፊት ፈጥነው ዮርዳኖስን ተሻገሩ። |
እነርሱም ንጉሡንና ተከታዮቹን በጀልባ አጅበው ወደ ማዶ ለማድረስና ንጉሡ የሚፈልገውን ሁሉ ለማድረግ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻገሩ። ንጉሡ ወንዙን ለመሻገር ሲዘጋጅ ሳለ የጌራ ልጅ ሺምዒ መጥቶ በፊቱ ተዘረጋና እንዲህ አለ፤
አንተ፥ ወንዶች ልጆችህና አገልጋዮችህ ለጌታህ ለሳኦል ቤተሰብ ምድሪቱን አርሳችሁ ምግብ ይሆናቸው ዘንድ መከሩን አገቡላቸው፤ የጌታህ የልጅ ልጅ መፊቦሼት ግን ዘወትር በገበታዬ የሚቀርብ ተመጋቢ ይሆናል፤” ጺባ ዐሥራ አምስት ወንዶች ልጆችና ኻያ አገልጋዮች ነበሩት።
ከሳኦል ቤተሰብ ጺባ የሚባል አንድ አገልጋይ ነበረ፤ እርሱም ወደ ዳዊት እንዲሄድ ተነገረው፤ ዳዊትም “አንተ ጺባ ነህን?” ሲል ጠየቀው። ጺባም “ጌታ ሆይ! እነሆ አገልጋይህ ነኝ!” ሲል መለሰ።
“ከዚህም ጋር መረሳት የሌለበት የብንያም ክፍል በሆነችው በባሑሪም ከተማ ውስጥ የሚኖረው የጌራ ልጅ ሺምዒ አለ፤ እርሱ ወደ ማሕናይም በሄድኩበት ቀን በእኔ ላይ የስድብ ውርጅብኝ አውርዶብኛል፤ ይሁን እንጂ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ባገኘኝ ጊዜ እንደማላስገድለው በእግዚአብሔር ስም ቃል ገብቼለት ነበር፤