2 ሳሙኤል 18:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአብ ጦርነቱ ይቆም ዘንድ እምቢልታ እንዲነፉ አዘዘ፤ ወታደሮቹም እስራኤላውያንን ከማሳደድ ተመልሰው መጡ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢዮአብ ቀንደ መለከት ነፍቶ ስለ ከለከላቸው፣ ሰራዊቱ እስራኤልን ማሳደዱን አቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአብም ቀንደ መለከት ነፋ፤ ሠራዊቱ እስራኤልን እንዳያሳድዱም ስለከለከለ ከማሳደድ ተመለሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብም ሕዝቡን ስለ ራራላቸው መለከት አስነፋ፤ ሕዝቡም እስራኤልን ተከትለው እንዳያሳድዱአቸው መለሳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም ሕዝቡን ከልክሎ ነበርና ቀንደ መለከት ነፋ፥ ሕዝቡም እስራኤልን ከማሳደድ ተመለሰ። |
ይህንንም ዕቅድ በተግባር ለመግለጥ ወደ ከተማይቱ ሕዝብ ሄደች፤ እነርሱም የቢክሪን ልጅ የሺባዕን ራስ ቈርጠው በግንቡ ላይ ለኢዮአብ ወረወሩለት፤ እርሱም ወታደሮቹ ከተማይቱን ለቀው ይወጡ ዘንድ ምልክት እንዲሆን እምቢልታ ነፋ፤ እነርሱም ወደየቤታቸው ተመለሱ፤ ኢዮዓብም ንጉሡን ለማግኘት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ።