2 ሳሙኤል 17:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ከሄዱ በኋላ አሒማዓጽና ዮናታን በፍጥነት ከጒድጓዱ ወጥተው በመሄድ የሆነውን ሁሉ ለንጉሥ ዳዊት ነገሩት፤ አኪጦፌል በእነርሱ ላይ ዐቅዶት የነበረውን ካስረዱት በኋላም “ፈጥነህ ወንዙን ተሻገር!” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቹ ከሄዱ በኋላ እነዚህ ሁለቱ ከጕድጓዱ ወጥተው ሄዱ፤ ለንጉሥ ዳዊትም፣ “አኪጦፌል በአንተ ላይ እንዲህ እንዲህ ብሎ ስለ መከረብህ ተነሥተህ በፍጥነት ወንዙን ተሻገር” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዎቹ ከሄዱ በኋላ ሁለቱም ከጉድጓዱ ወጥተው ሄዱ፤ ለንጉሥ ዳዊትም፥ “አኪጦፌል በአንተ ላይ እንዲህ እንዲህ ብሎ ስለመከረብህ ተነሥተህ በፍጥነት ወንዙን ተሻገር” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሄዱም በኋላ እነርሱ ከጕድጓዱ ወጥተው ሄዱ፤ ለንጉሡም ለዳዊት ነገሩት፤ ዳዊትንም፥ “አኪጦፌል በእናንተ ላይ እንዲህ መክሮአልና ተነሡ፤ ፈጥናችሁም ውኃውን ተሻገሩ” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሄዱም በኋላ እነርሱ ከጉድጓዱ ወጥተው ሄዱ፥ ለንጉሡም ለዳዊት ነገሩት፥ ዳዊትንም፦ አኪጦፌል በእናንተ ላይ እንዲህ መክሮአልና ተነሡ፥ ፈጥናችሁም ውኃውን ተሻገሩ አሉት። |