ኢዮአብም በዳዊት ፊት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት በአክብሮት ንጉሡን አመሰገነ፤ “የፈለግኹትን እንዳደርግ በመፍቀድህ በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን አሁን ተረዳሁ” አለ።
2 ሳሙኤል 16:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም ጺባን “የመፊቦሼት የነበረው ንብረት ሁሉ ከእንግዲህ የአንተ ነው” አለው። ጺባም “ንጉሥ ሆይ! እነሆ እኔ አገልጋይህ ነኝ፤ ዘወትር አንተን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ለመሥራት እተጋለሁ!” ሲል መለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ንጉሡ ሲባን፣ “የሜምፊቦስቴ የነበረው ሁሉ ከእንግዲህ ያንተ ነው” አለው። ሲባም፣ “በታላቅ ትሕትና በግንባሬ ተደፍቼ እጅ እነሣለሁ፤ ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ በፊትህ ሞገስ ላግኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ንጉሡ ጺባን፥ “የመፊቦሼት የነበረው ሁሉ ከእንግዲህ ያንተ ነው” አለው። ጺባም፥ “እጅ እነሣለሁ፤ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ በፊትህ ሞገስ ላግኝ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ሲባን፥ “እነሆ፥ ለሜምፌቡስቴ የነበረው ሁሉ ለአንተ ይሁን” አለው። ሲባም ሰግዶ፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በፊትህ ሞገስን ላግኝ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ሲባን፦ እነሆ፥ ለሜምፊቦስቴ የነበረው ሁሉ ለአንተ ይሁን አለው። ሲባም፦ እጅ እነሣለሁ፥ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በፊትህ ሞገስ ላግኝ አለ። |
ኢዮአብም በዳዊት ፊት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት በአክብሮት ንጉሡን አመሰገነ፤ “የፈለግኹትን እንዳደርግ በመፍቀድህ በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን አሁን ተረዳሁ” አለ።
ንጉሡም “የጌታህ የሳኦል የልጅ ልጅ መፊቦሼት የት ነው?” ሲል ጠየቀው። ጺባም “እስራኤላውያን የአያቱን የሳኦልን መንግሥት መልሰው እንደሚሰጡት ስለ ተማመነ እርሱ አሁን የሚገኘው በኢየሩሳሌም ነው” ሲል መለሰ።
ንጉሥ ሆይ! እንዲያውም ስለ እኔ በውሸት ለአንተ የነገረህ ጉዳይ አለ፤ ነገር ግን አንተ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለ ሆንክ መልካም መስሎ የታየህን አድርግ።
የሳኦል የልጅ ልጅ፥ የዮናታን ልጅ መፊቦሼት በመጣ ጊዜ በዳዊት ፊት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት አክብሮቱን ገለጠ። ዳዊትም “መፊቦሼት!” ሲል ጠራው። መፊቦሼትም “ጌታ ሆይ! እነሆ አገልጋይህ ነኝ!” ሲል መለሰ።
ከዚህ በኋላ ንጉሡ የሳኦልን አገልጋይ ጺባን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “የሳኦልና የቤተሰቡ ንብረት የነበረውን ማናቸውንም ነገር የጌታህ የልጅ ልጅ ለሆነው ለመፊቦሼት እሰጣለሁ፤
“የአንድን ሰው ወንጀለኛነት ለማረጋገጥ አንድ ምስክር ብቻ አይበቃም፤ አንድ ሰው ወንጀለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ ሁለት ወይም ሦስት ምስክሮች ያስፈልጋሉ።