ንግግሩንም በመቀጠል ሳዶቅን እንዲህ አለው፤ “ተመልከት፤ ልጅህን አሒማዓጽንና የአብያታርንም ልጅ ዮናታንን ይዘህ ወደ ከተማይቱ በሰላም ሂድ፤
2 ሳሙኤል 15:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱም ጋር ልጆቻቸው አሒማዓጽና ዮናታን ይገኛሉ፤ የምታገኘውንም ወሬ ሁሉ በእነርሱ በኩል ልትልክብኝ ትችላለህ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሳዶቅ ልጅ አኪማአስና የአብያታር ልጅ ዮናታን፣ ሁለቱ ወንዶች ልጆቻቸው እዚያው ዐብረዋቸው ይገኛሉ። የምትሰማትን ሁሉ በእነርሱ ላክልኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ የሳዶቅ ልጅ አሒማአስና የአብያታር ልጅ ዮናታን፥ ሁለቱ ወንዶች ልጆቻቸው እዚያው አብረዋቸው ይገኛሉ። የምትሰማትን ሁሉ በእነርሱ ላክልኝ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ የሳዶቅ ልጅ አኪማኦስና የአብያታር ልጅ ዮናታን፥ ልጆቻቸው በዚያ ከእነርሱ ጋር አሉ፤ የምትሰሙትን ሁሉ በእነርሱ እጅ ላኩልኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ የሳዶቅ ልጅ አኪማአስና የአብያታር ልጅ ዮናታን ልጆቻቸው በዚያ ከእነርሱ ጋር አሉ፥ የምትሰሙትን ሁሉ በእነርሱ እጅ ላኩልኝ። |
ንግግሩንም በመቀጠል ሳዶቅን እንዲህ አለው፤ “ተመልከት፤ ልጅህን አሒማዓጽንና የአብያታርንም ልጅ ዮናታንን ይዘህ ወደ ከተማይቱ በሰላም ሂድ፤
የአብያታር ልጅ ዮናታንና የሳዶቅ ልጅ አሒማዓጽ ወደ ከተማይቱ ሲገቡ ማንም እንዳያያቸው ስለ ፈሩ፥ ከኢየሩሳሌም አካባቢ ባለችው በዔንሮጌል ምንጭ አጠገብ ይጠባበቁ ነበር፤ አንዲት ልጃገረድ አገልጋይም ዘወትር ወደዚያ እየሄደች የሚሆነውን ነገር ሁሉ ትነግራቸው ነበር፤ ከዚያም በኋላ እነርሱ ሄደው ለንጉሥ ዳዊት ይነግሩት ነበር።
እርሱ ገና ተናግሮ ሳይጨርስ የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን ድንገት ደረሰ፤ አዶንያስም “እስቲ ና ግባ፤ አንተ ጥሩ ሰው ስለ ሆንክ መልካም ዜና ይዘህ ሳትመጣ አትቀርም” አለው።