La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 14:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሴቲቱም ወደ ንጉሡ ቀርባ ወደ መሬት ለጥ ብላ እጅ ነሣችና “ንጉሥ ሆይ! እባክህ እርዳኝ!” አለችው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የቴቁሔዪቱም ሴት ወደ ንጉሡ ገብታ፣ በንጉሡ ፊት ወደ መሬት በግምባሯ ተደፍታ እጅ በመንሣት አክብሮቷን ከገለጠች በኋላ፣ “ንጉሥ ሆይ! እርዳኝ” አለች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የተቆዓዪቱም ሴት ወደ ንጉሡ ገብታ፥ በንጉሡ ፊት በግምባሯ በምድር ላይ ተደፍታ እጅ በመንሣት፥ “ንጉሥ ሆይ! እርዳኝ” አለች።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲ​ሁም የቴ​ቁ​ሔ​ዪቱ ሴት ወደ ንጉሥ ገብታ በግ​ን​ባ​ርዋ በም​ድር ላይ ወደ​ቀች፤ ሰግ​ዳም “ንጉሥ ሆይ፥ አድ​ነኝ፤ አድ​ነኝ” አለች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንዲሁም የቴቁሔይቱ ሴት ወደ ንጉሥ ገብታ በግምባርዋ በምድር ላይ ወደቀች፥ እጅ ነሥታም፦ ንጉሥ ሆይ፥ አድነኝ አለች።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 14:4
9 Referencias Cruzadas  

በሦስተኛው ቀን አንድ ወጣት ከሳኦል ሰፈር መጣ፤ ልብሱን ቀዶ በራሱ ላይ ትቢያ ነስንሶ ነበር፤ ወደ ዳዊትም ቀርቦ በአክብሮት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ፤


ኢዮአብም በዳዊት ፊት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት በአክብሮት ንጉሡን አመሰገነ፤ “የፈለግኹትን እንዳደርግ በመፍቀድህ በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን አሁን ተረዳሁ” አለ።


ንጉሡም “ምን ችግር አጋጠመሽ?” አላት፤ እርስዋም እንዲህ ስትል መለሰች፦ “እኔ ባሌ የሞተብኝ መበለት ሴት ነኝ፤


አሒማዓጽም ድምፁን ከፍ አድርጎ ለንጉሡ ሰላምታ ሰጠ፤ በንጉሡም ፊት በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ “ንጉሥ ሆይ! በአንተ ላይ በዐመፅ የተነሣሡትን ድል እንድታደርግ ስለ ረዳህ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!” አለ።


ልጁም ከሄደ በኋላ ዳዊት ከድንጋዩ ቊልል በስተኋላ ከተደበቀበት ስፍራ ወጥቶ በጒልበቱ በመንበርከክ ሦስት ጊዜ ወደ መሬት ሰገደ፤ እርሱና ዮናታን በሚሳሳሙበት ጊዜ ሁለቱም ያለቅሱ ነበር፤ ከዮናታንም ይልቅ የዳዊት ሐዘን የበረታ ነበር።


አቢጌልም ዳዊትን ባየችው ጊዜ በፍጥነት ከአህያዋ ወርዳ በዳዊት ጫማ አጠገብ መሬት ላይ ለጥ ብላ እጅ ነሣች፤