2 ሳሙኤል 14:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ ዳዊት አቤሴሎምን እንደ ናፈቀ የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ ተረዳ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የንጉሡ ልብ አቤሴሎምን እንደ ናፈቀ ተረዳ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንጉሡ ልብ አቤሴሎምን እንደናፈቀ የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ ተረዳ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሶርህያ ልጅ ኢዮአብም የንጉሡ ልብ ወደ አቤሴሎም እንዳዘነበለ ዐወቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጽሩያም ልጅ ኢዮአብ የንጉሡ ልብ ወደ አቤሴሎም እንዳዘነበለ አወቀ። |
ስለዚህም በተቆዓ የምትኖረውን አንዲት ብልኅ ሴት አስጠራ፤ እርስዋም በደረሰች ጊዜ “ሐዘንተኛ ለመምሰል ሞክሪ፤ የሐዘን ልብስሽን ልበሺ፤ ቅቤም አትቀቢ፤ ለብዙ ጊዜ በሐዘን ላይ የቈየሽ ሴት ለመምሰል ተዘጋጂ፤
ንጉሡም እጅግ አዘነ፤ በቅጽር በሩ አናት ላይ ወደሚገኘውም ክፍል ወጥቶ አለቀሰ፤ ወደዚያም ሲመጣ “ልጄ ሆይ! ልጄ አቤሴሎም! አቤሴሎም ልጄ! ምነው በአንተ ምትክ እኔ በሞትኩ ልጄ ሆይ! አቤሴሎም ልጄ!” እያለ በመጮኽ ያለቅስ ነበር።
እንዲሁም ንጉሡ በልጁ ሞት ምክንያት በሐዘን ላይ መሆኑን ስለ ሰሙ ወታደሮቹ ያገኙት የድል አድራጊነት ደስታ በዚያ ቀን ወደ ሐዘን ተለወጠባቸው።