2 ሳሙኤል 13:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም ወደ ወንድምዋ ወደ አምኖን ቤት በሄደች ጊዜ አልጋ ላይ ተኝቶ አገኘችው፤ ጥቂት ሊጥ ወስዳ በማቅጠንም አምኖን እያያት እንጀራ ጋገረች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ትዕማር ወንድሟ አምኖን ወደ ተኛበት ቤት ሄደች፤ ጥቂት ሊጥ ወስዳ ካቦካች በኋላ እያየ አዘጋጅታ ጋገረችው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ትዕማር ወንድሟ አምኖን ወደ ተኛበት ቤት ሄደች፤ ጥቂት ሊጥ ወስዳ ካቦካች በኋላ እያየ ጋገረችው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትዕማርም ወደ ወንድምዋ ወደ አምኖን ቤት ሄደች፤ ተኝቶም ነበር፤ ዱቄትም ወስዳ ለወሰች፤ በፊቱም እንጎቻ አደረገች፤ ጋገረችም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትዕማርም ወደ ወንድምዋ ወደ አምኖን ቤት ሄደች፥ ተኝቶም ነበር፥ ዱቄትም ወስዳ ለወሰች፥ እያየም እንጎቻ አደረገች፥ ጋገረችም። |
የጋገረችውንም እንጀራ ከምጣዱ አውጥታ እንዲበላ አቀረበችለት፤ እርሱ ግን መመገቡን እምቢ ብሎ “ሰዎቹን ሁሉ አስወጡልኝ” አለ፤ ሁሉም ወጡ፤
“ ‘ከእኅቱ ወይም በአንድ በኩል ብቻ እኅቱ ከሆነች ሴት ጋር ግንኙነት የሚፈጽም ወንድ ሁሉ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይበሉ።