2 ሳሙኤል 13:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ አገልጋዮቹ አቤሴሎም በነገራቸው መመሪያ መሠረት አምኖንን ገደሉ፤ የቀሩትም የዳዊት ወንዶች ልጆች በበቅሎዎቻቸው ተቀምጠው እየጋለቡ ሸሹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአቤሴሎምም አገልጋዮች ጌታቸው ያዘዛቸውን በአምኖን ላይ ፈጸሙ። ከዚያም የንጉሡ ልጆች በሙሉ ተነሥተው በየበቅሎዎቻቸው ላይ ተቀምጠው ሸሹ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአቤሴሎምም አገልጋዮች በአምኖን ላይ አቤሴሎም ያዘዛቸውን ፈጸሙ። ከዚያም የንጉሡ ልጆች በሙሉ ተነሥተው በየበቅሎዎቻቸው ላይ ተቀምጠው ሸሹ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአቤሴሎምም አገልጋዮች አቤሴሎም እንዳዘዛቸው በአምኖን ላይ አደረጉበት። የንጉሡም ልጆች ሁሉ ተነሥተው በየበቅሎዎቻቸው ተቀምጠው ሸሹ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአቤሴሎምም አገልጋዮች አቤሴሎም እንዳዘዛቸው በአምኖን ላይ አደረጉበት። የንጉሡም ልጆች ሁሉ ተነሥተው በየበቅሎቻቸው ተቀምጠው ሸሹ። |
ወደ ቤታቸው ለመድረስ ገና በመንገድ ላይ ሳሉ “አቤሴሎም ልጆችህን ሁሉ ገደላቸው! አንድ እንኳ የቀረ የለም!” የሚል ወሬ ለዳዊት ደረሰው።
ንጉሥ ሆይ! እኔ አገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ አንድ ቀን ገላጋይ በሌለበት ስፍራ ሁለቱ ልጆቼ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፤ አንዱ ሌላውን ገደለው፤
በድንገት፥ አቤሴሎም ከዳዊት ተከታዮች ጥቂቱን አገኘ፤ አቤሴሎም በዚያን ጊዜ በበቅሎ ላይ ተቀምጦ ይጋልብ ስለ ነበር በቅሎዋ በአንድ ትልቅ የወርካ ዛፍ ሥር ስታልፍ ሳለ የዛፉ ቅርንጫፍ የአቤሴሎምን ራስ ጠጒር ያዘበት፤ በቅሎዋም በእግሮቹ መኻል ሾልካ ስትሄድ አቤሴሎም በዐየር ላይ ተንጠልጥሎ ቀረ።
ንጉሡም እንዲህ አላቸው፦ “በቤተ መንግሥቴ ከሚገኙት ባለሟሎቼ ጋር አብራችሁ ሂዱ፤ ልጄን ሰሎሞንንም እኔ በምቀመጥባት በቅሎ አስቀምጡትና አጅባችሁት ወደ ግዮን ምንጭ ውረዱ፤
ስለዚህ ካህኑ ሳዶቅ፥ ነቢዩ ናታን፥ የዮዳሄ ልጅ በናያና የንጉሡ ክብር ዘበኞች ሰሎሞንን ዳዊት በሚቀመጥባት በቅሎ ላይ በማስቀመጥ ወደ ግዮን ምንጭ ወረዱ፤
“ትእዛዞቼን ጠብቁ፤ አንዱን እንስሳ ከሌላው ጋር አታዳቅል፥ በአንድ እርሻ ላይ ሁለት ዐይነት እህል አትዝራ፥ ከሁለት ዐይነት ነገር ተፈትሎ የተሠራ ልብስ አትልበስ።
እጆቻቸው ክፉ ነገርን ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ባለ ሥልጣኑና ዳኛው ጉቦ ይጠይቃሉ፤ ኀይለኛ ፍላጎቱን በግዴታ ተግባራዊ ያስደርጋል፤ በዚህም ዐይነት ሁሉም ፍርድን ያጣምማሉ።