ይሁን እንጂ ለእኔ ታማኞች የሆኑ፥ ለባዓል ያልሰገዱና ምስሉንም ያልተሳለሙ ሰባት ሺህ ሰዎችን በእስራኤል ምድር በሕይወት እንዲተርፉ አደርጋለሁ።”
2 ነገሥት 5:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም የሀገሬን ንጉሥ በማጀብ ሪሞን የተባለ የሶርያ አምላክ ወደሚመለክበት መቅደስ ብገባና ብሰግድም እንኳ እግዚአብሔር ይቅር እንደሚለኝ ተስፋ አደርጋለሁ፤ በእርግጥም ይቅር ይለኛል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እግዚአብሔር ስለ አንድ ነገር ብቻ አገልጋይህን ይቅር ይበለው፤ ይኸውም ጌታዬ ለመስገድ ወደ ሬሞን ቤተ ጣዖት በሚገባበት ጊዜ ክንዴን ሲደገፍ እኔም እንደ እርሱ በዚያ ብሰግድ፣ በሬሞን ቤተ ጣዖት በመስገዴ እግዚአብሔር አገልጋይህን ይቅር ይበለው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም የሀገሬን ንጉሥ በማጀብ ሪሞን የተባለ የሶርያ አምላክ ወደሚመለክበት መቅደስ ብገባና ብሰግድም እንኳ እግዚአብሔር ይቅር እንደሚለኝ ተስፋ አደርጋለሁ፤ በእርግጥም ይቅር ይለኛል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም የእኔን የአገልጋይህን ኀጢአት በዚህ ነገር ብቻ ይቅር ይበለኝ፤ ጌታዬ በዚያ ይሰግድ ዘንድ እጄን ተደግፎ ወደ ሬማን ቤት በገባና በሰገደ ጊዜ፥ እኔም በሬማን ቤት በሰገድሁ ጊዜ፥ እግዚአብሔር በዚህ ነገር እኔን አገልጋይህን ይቅር ይለኛል” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ለእኔ ለባሪያህ በዚህ ነገር ብቻ ይቅር ይበለኝ፤ ጌታዬ በዚያ ይሰግድ ዘንድ እጄን ተደግፎ ወደ ሬሞን ቤት በገባ ጊዜ፥ እኔም በሬሞን ቤት በሰገድሁ ጊዜ፥ እግዚአብሔር በዚህ ነገር ለእኔ ለባሪያህ ይቅር ይበለኝ፤” አለ። |
ይሁን እንጂ ለእኔ ታማኞች የሆኑ፥ ለባዓል ያልሰገዱና ምስሉንም ያልተሳለሙ ሰባት ሺህ ሰዎችን በእስራኤል ምድር በሕይወት እንዲተርፉ አደርጋለሁ።”
እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን በመግባት እስራኤላውያንን እንዲህ ሲል አዞአቸው ነበር፤ “ባዕዳን አማልክትን አታምልኩ፤ ለእነርሱም አገልጋዮች በመሆን አትስገዱላቸው፤ መሥዋዕትንም አታቅርቡላቸው፤
በዚህም ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ የከተማይቱ ቅጽር በር የቅርብ ባለሟሉ በሆነው አገልጋዩ ኀላፊነት ሥር እንዲጠበቅ አድርጎ ነበር፤ ነገር ግን ያንን አገልጋይ ሕዝቡ ስለ ረጋገጠው በዚያ ሞተ፤ ይህም የሆነው ንጉሡ ኤልሳዕን ለማነጋገር በሄደ ጊዜ ኤልሳዕ በዚያ አገልጋይ ላይ የተናገረበት የትንቢት ቃል ስለ ተፈጸመ ነው።
በዚህ ጊዜ የንጉሡ የቅርብ ባለሟል የሆነ አገልጋዩ ኤልሳዕን፥ “እግዚአብሔር ራሱ የሰማይ መስኮቶችን ከፍቶ እህልን እንደ ዝናብ ቢያዘንብ እንኳ ይህ ሊሆን ከቶ አይችልም!” ሲል በመጠራጠር ተናገረ። ኤልሳዕም “ያን እህል በዐይንህ ታያለህ፤ ነገር ግን ከእርሱ ምንም ነገር አትቀምስም!” አለው።
እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እጅግ ቀናተኛ ስለ ሆንኩ ተቀርጾ የተሠራውን ማንኛውም ጣዖት አታምልክ፤ አትስገድለትም፤ እኔ የሚጠሉኝን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዘራቸውንም ሁሉ እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ እበቀላለሁ።
በመካከላችሁ ከቀሩት ሕዝቦች ጋር ከቶ አትተባበሩ፤ የአማልክታቸውንም ስም አትጥሩ፤ በእነርሱም አትማሉ፤ ለእነርሱም አገልጋዮች አትሁኑ፤ አትስገዱላቸውም።