የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ‘እኔ እግዚአብሔር ዝናብን እስከማወርድ ድረስ ዱቄቱ ከማኖሪያው ዕቃ፥ ዘይቱም ከማሰሮው ከቶ አያልቅም’ ሲል ተናግሮአል።”
2 ነገሥት 4:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማድጋዎቹንም ሁሉ ከሞሉ በኋላ “ሌላ ትርፍ የለም ወይ?” ስትል ጠየቀች፤ ከልጆችዋም አንዱ “ሌላ ማድጋ የለም” ሲል መለሰላት። ከዚያም በኋላ ዘይቱ መውረዱን አቆመ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማድጋዎቹ ሁሉ ከሞሉ በኋላ ልጇን፣ “ሌላ ማድጋ አምጣ” አለችው። እርሱ ግን፣ “ምንም የቀረ ማድጋ የለም” ሲል መለሰላት። ከዚያም ዘይቱ መውረዱን አቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማድጋዎቹንም ሁሉ ከሞሉ በኋላ “ሌላ ትርፍ የለም ወይ?” ስትል ጠየቀች፤ ከልጆችዋም አንዱ “ሌላ ማድጋ የለም” ሲል መለሰላት። ከዚያም በኋላ ዘይቱ መውረዱን አቆመ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ልጆችዋን፥ “ደግሞ ማድጋ አምጡልኝ” አለቻቸው፤ እነርሱም፥ “ሌላ ማድጋ የለም” አሏት፤ ዘይቱም ቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማድጋዎቹም በሞሉ ጊዜ ልጅዋን “ደግሞም ማድጋ አምጣልኝ፤” አለችው፤ እርሱም “ሌላ ማድጋ የለም፤” አላት፤ ዘይቱም ቆመ። |
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ‘እኔ እግዚአብሔር ዝናብን እስከማወርድ ድረስ ዱቄቱ ከማኖሪያው ዕቃ፥ ዘይቱም ከማሰሮው ከቶ አያልቅም’ ሲል ተናግሮአል።”
ይህም ኤልሳዕን አስቈጣው፤ ስለዚህም ንጉሡን “አምስት ወይም ስድስት ጊዜ መተህ ቢሆን ኖሮ በሶርያውያን ላይ ፍጹም ድልን ትቀዳጅ ነበር፤ አሁን ግን ሦስት ጊዜ ብቻ ድል ትነሣቸዋለህ” አለው።
ስለዚህም ሴትዮዋ ወደ ቤትዋ ሄዳ ከልጆችዋ ጋር በሩን ዘጋች፤ ዘይት የነበረበትን ትንሽ ማሰሮ አንሥታ ልጆችዋ እያቀረቡላት በማንቈርቈር በየማድጋዎቹ ሞላች።
ከምድሪቱ የሚገኘውን ምግብ መብላት ከጀመሩበት ቀን አንሥቶ መና መዝነቡን አቋረጠ፤ እስራኤላውያንም ከዚያን በኋላ ያን መና ማግኘት አልቻሉም፤ ከዚያን ጊዜ አንሥቶ በከነዓን የበቀለውን እህል መብላት ጀመሩ።