ጥቂት ሰዎች ከኢያሪኮ ወደ ኤልሳዕ መጥተው “ጌታችን አንተ እንደምታውቀው ይህች ምድር መልካም ናት፤ ውሃው ግን መጥፎ በመሆኑ ምድሪቱ ምርት አትሰጥም” አሉት።
2 ነገሥት 2:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልሳዕም “በአዲስ አፍላል ማሰሮ ውስጥ ጨው ጨምራችሁ አምጡልኝ” ብሎ አዘዘ። እነርሱም እንዳዘዛቸው አድርገው አመጡለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “እስኪ በአዲስ ማሰሮ ጨው ጨምራችሁ አምጡልኝ” አለ፤ እንዳለውም አመጡለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልሳዕም “በአዲስ አፍላል ማሰሮ ውስጥ ጨው ጨምራችሁ አምጡልኝ” ብሎ አዘዘ። እነርሱም እንዳዘዛቸው አድርገው አመጡለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “አዲስ ማሰሮ አምጡልኝ፤ ጨውም ጨምሩበት” አለ፤ ያንም አመጡለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም “አዲስ ማሰሮ አምጡልኝ፤ ጨውም ጨምሩበት፤” አለ፤ ያንንም አመጡለት። |
ጥቂት ሰዎች ከኢያሪኮ ወደ ኤልሳዕ መጥተው “ጌታችን አንተ እንደምታውቀው ይህች ምድር መልካም ናት፤ ውሃው ግን መጥፎ በመሆኑ ምድሪቱ ምርት አትሰጥም” አሉት።
እርሱም ወደ ምንጩ ሄዶ ጨውን በውሃው ውስጥ በመጨመር፥ “እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው ‘እኔ ይህን ውሃ በመፈወስ ንጹሕ እንዲሆን አደርጋለሁ፤ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ የሞትና የምርት አልባነት ምክንያት አይሆንም’ ” ሲል ተናገረ፤
እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ፥ ሞአብ እንደ ሰዶም አሞንም እንደ ገሞራ ይሆናሉ፤ ምድሪቱም በዳዋና በጨው ጒድጓድ ተወራ ለዘለቄታ ባድማ ትሆናለች፤ ከሞት የተረፈው ሕዝቤ ይበዘብዛቸዋል ንብረታቸውንም ይወርሳል።”