2 ነገሥት 17:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ከጥቂት ዓመቶች በኋላ ንጉሥ ሆሴዕ፥ ሶእ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ግብጽ ንጉሥ መልእክተኞች በመላክ ይረዳው ዘንድ ጠየቀ፤ በየዓመቱ ለአሦር ንጉሥ ይሰጠው የነበረውንም ግብር አቆመ፤ ሰልምናሶር ይህን በሰማ ጊዜ ሆሴዕን አስይዞ ወህኒ ቤት አስገባው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአሦር ንጉሥ ግን ሆሴዕ እንደ ከዳው ተገነዘበ፤ ምክንያቱም ወደ ግብጽ ንጉሥ ወደ ሲጎር መልክተኞች ስለ ላከና በየዓመቱም ያደርግ እንደ ነበረው ለአሦር ንጉሥ ስላልገበረ ነው፤ ከዚህም የተነሣ ስልምናሶር ይዞ ወህኒ ቤት አስገባው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ከጥቂት ዓመቶች በኋላ ንጉሥ ሆሴዕ፥ ሶእ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ግብጽ ንጉሥ መልእክተኞች በመላክ ይረዳው ዘንድ ጠየቀ፤ በየዓመቱ ለአሦር ንጉሥ ይሰጠው የነበረውንም ግብር አቆመ፤ ሰልምናሶር ይህን በሰማ ጊዜ ሆሴዕን አስይዞ ወህኒ ቤት አስገባው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሦርም ንጉሥ በሆሴዕ ላይ ዐመፅ አገኘ፤ መልእክተኞችን ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ሴጎር ልኮ ነበርና፤ እንደ ልማዱም በየዓመቱ ለአሦር ንጉሥ ግብር አልሰጠምና፤ ስለዚህ የአሦር ንጉሥ ተዋጋው፤ ይዞም በወህኒ ቤት አሰረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሦርም ንጉሥ በሆሴዕ ላይ ዐመፅ አገኘ፤ መልእክተኞችን ወደ ግብጽ ንጉሥ ወደ ሴጎር ልኮ ነበርና፤ እንደ ልማዱም በየዓመቱ ለአሦር ንጉሥ ግብር አልሰጠምና፤ ስለዚህ የአሦር ንጉሥ ይዞ በወህኒ ቤት አሰረው። |
የግብጽ ንጉሥ ይረዳኛል ብለህ አስበህ ከሆነ፥ የተቀጠቀጠ ሸምበቆ እንደሚመረኰዝ ሰው መሆንህ ነው፤ እርሱ ተሰብሮ ስንጣሪው እጅህን ያቈስልሃል፤ እንግዲህ የግብጽ ንጉሥ ለሚተማመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው’ ሲል የአሦር ንጉሠ ነገሥት ይጠይቅሃል።”
ይኸውም ሴዴቅያስ ዐይኑ እያየ ልጆቹ በፊቱ ታረዱ፤ ከዚህም በኋላ ናቡከደነፆር የሴዴቅያስን ዐይኖች አውጥቶ አሳወረው፤ እጆቹንም በሰንሰለት አስሮ ወደ ባቢሎን ወሰደው።
ሕዝቅያስ ‘አምላካችን እግዚአብሔር ከአሦራውያን እጅ ያድነናል’ ይላችኋል፤ ነገር ግን እርሱ እንደዚህ ባለ አነጋገር እያታለለ፥ በራብና በውሃ ጥም እንድታልቁ ሊያደርጋችሁ ነው፤
በሐሰት መሐላ ቃል ኪዳን በመግባት ከንቱ ንግግር ይናገራሉ፤ ስለዚህ በእርሻ መሬት ውስጥ መርዘኛ አረም እንደሚበቅል በእነርሱም መካከል ክርክር ይስፋፋል።
እግዚአብሔር በይሁዳ ሕዝብ ላይ የሚያቀርበው ወቀሳ አለው፤ የያዕቆብንም ልጆች እንደ አካሄዳቸው ይቀጣቸዋል፤ ባደረጉትም ክፉ ሥራ መጠን ዋጋቸውን ይከፍላቸዋል።
መንግሥታትን ለመለማመጥ ዋጋ ቢከፍሉም እንኳ እኔ በአንድነት እሰበስበዋለሁ፤ ነገሥታትና መሳፍንት በሚያደርጉባቸው ጭቈና እየመነመኑ ይሄዳሉ።
“እግዚአብሔር አንተንና ንጉሥህን ከዚህ በፊት የቀድሞ አባቶችህም ሆኑ አንተ ወዳልነበራችሁበት ባዕድ አገር አፍልሶ ይወስዳችኋል፤ በዚያም ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ባዕዳን አማልክትን ታመልካላችሁ።