2 ነገሥት 14:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሜስያስ መንግሥቱን አደላድሎ እንደ ያዘ ወዲያውኑ፥ ቀደም ሲል ነግሦ የነበረውን አባቱን የገደሉትን ባለሥልጣኖች በሞት ቀጣ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንግሥቱም በእጁ ከጸናለት በኋላ፣ ንጉሡን አባቱን የገደሉትን ሹማምት ገደላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሜስያስ መንግሥቱን አደላድሎ እንደ ያዘ ወዲያውኑ፥ ቀደም ሲል ነግሦ የነበረውን አባቱን የገደሉትን ባለ ሥልጣኖች በሞት ቀጣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንግሥቱም በእጁ በጸናለት ጊዜ አባቱን የገደሉትን አገልጋዮች ገደለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንግሥቱም በጸናለት ጊዜ አባቱን የገደሉትን ባሪያዎች ገደለ። |
የአሦር ንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴር እስራኤልን ወረረ፤ ምናሔም በአገሩ መንግሥት ላይ ሥልጣኑን እንዲያጸናለትና እንዲደግፈው ለመማጠን ሠላሳ አራት ሺህ ኪሎ የሚመዝን ብር እጅ መንሻ አድርጎ ለቲግላት ፐሌሴር ሰጠው።
ይህን ብታደርጉ የምትኖሩበትን ምድር ታረክሳላችሁ፤ የነፍስ ግድያ ወንጀል ምድሪቱን ያረክሳል፤ ስለዚህ የነፍሰ ገዳዩ ደም ካልፈሰሰ በቀር ምድሪቱን ከደም ለማንጻት የሚፈጸም ሌላ ሥርዓት የለም።