በዚህም ዐይነት ጣዖት አምላኪዎቹ የተቀደሰ ነው ብለው የሚያምኑበትን የድንጋይ ዐምድና ቤተ መቅደሱን አፈራረሱ፤ ቤተ መቅደሱንም መጸዳጃ አደረጉት፤ ዛሬም በዚሁ ዐይነት ይገኛል።
2 ነገሥት 10:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዩ በእስራኤል የነበረውን የባዓልን ጣዖታዊ አምልኮ ያስወገደው በዚህ ዐይነት ዘዴ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ሁኔታም ኢዩ የበኣልን አምልኮ ከእስራኤል አስወገደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዩ በእስራኤል የነበረውን የበዓልን ጣዖታዊ አምልኮ ያስወገደው በዚህ ዓይነት ዘዴ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም ኢዩ በዓልን ከእስራኤል አጠፋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም ኢዩ በኣልን ከእስራኤል አጠፋ። |
በዚህም ዐይነት ጣዖት አምላኪዎቹ የተቀደሰ ነው ብለው የሚያምኑበትን የድንጋይ ዐምድና ቤተ መቅደሱን አፈራረሱ፤ ቤተ መቅደሱንም መጸዳጃ አደረጉት፤ ዛሬም በዚሁ ዐይነት ይገኛል።
ነገር ግን ኢዩ እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራውን የንጉሥ ኢዮርብዓምን የኃጢአት መንገድ ከመከተል አልተገታም፤ ኢዩ ራሱ ቀደም ሲል የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በቤትኤልና በዳን ላቆማቸው የወርቅ ጥጃ ምስሎች መስገዱ አልቀረም።