እነርሱ በእኔ ምትክ ለመሞት እንኳ የተዘጋጁ ነበሩ፤ በዚህም ዘወትር አመሰግናቸዋለሁ፤ እኔም ብቻ ሳልሆን ከአሕዛብነት ወደ ክርስትና የተመለሱ ምእመናን አብያተ ክርስቲያን ጭምር ያመሰግኑአቸዋል።
2 ቆሮንቶስ 8:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በወንጌል ስብከቱ በአብያተ ክርስቲያን ሁሉ የተመሰገነውን ወንድም ከእርሱ ጋር እንልካለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱም ጋራ በወንጌል ስብከት በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የተመሰገነውን ወንድም ልከነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም ጋር ስለ ወንጌል ስብከት በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የተመሰገነውን ወንድም እንልካለን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ወንጌል ትምህርት አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያመሰገኑትን ወንድማችንንም ከእርሱ ጋር ልከናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም ጋር ስለ ወንጌል ስብከት በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የተመሰገነውን ወንድም እንልካለን፤ |
እነርሱ በእኔ ምትክ ለመሞት እንኳ የተዘጋጁ ነበሩ፤ በዚህም ዘወትር አመሰግናቸዋለሁ፤ እኔም ብቻ ሳልሆን ከአሕዛብነት ወደ ክርስትና የተመለሱ ምእመናን አብያተ ክርስቲያን ጭምር ያመሰግኑአቸዋል።
እኔ ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ እናንተ የምትመርጥዋቸውን ሰዎች ያዋጣችሁትን ገንዘብ ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄዱ ከመሸኛ ደብዳቤ ጋር እልካቸዋለሁ።
በዚህ ምክንያት የተወደደውንና የታመነውን በጌታ ልጄ የሆነውን ጢሞቴዎስን ልኬላችኋለሁ፤ በየቦታውና በየአብያተ ክርስቲያኑ እንደማስተምረው እርሱ እኔ በክርስቶስ ያገኘሁትን የአዲስ ሕይወት መመሪያ ያሳስባችኋል።
እያንዳንዱ ጌታ በሰጠው ስጦታና እግዚአብሔር በጠራው ጊዜ በነበረበት ሁኔታ ይኑር፤ ለአብያተ ክርስቲያን ሁሉ የሰጠሁት መመሪያ ይህንኑ ነው።
ቲቶ ወደ እናንተ እንዲመጣ ለመንኩት፤ ያንን ወንድማችንንም ከእርሱ ጋር ላክሁት፤ ታዲያ፥ ቲቶስ ተጠቀመባችሁን? እኔና እርሱ ያገለገልናችሁ በአንድ መንፈስ አልነበረምን? አካሄዳችንስ አንድ አልነበረምን?
ከዚህም በላይ ይህ ወንድም እኛ ይህን በጎ ሥራ ለጌታ ክብር ስንፈጽምና ለማገልገል ያለንንም መልካም ፈቃድ ስንገልጥ አብሮን በመሄድ የሥራ ተካፋያችን እንዲሆን በአብያተ ክርስቲያን የተመረጠ ነው።