2 ቆሮንቶስ 4:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ተስፋ አንቈርጥም፤ ምንም እንኳ የውጪው ሰውነታችን ቢጠፋ የውስጡ ሰውነታችን በየቀኑ ይታደሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ተስፋ አንቈርጥም፤ ውጫዊው ሰውነታችን እየጠፋ ቢሄድም እንኳ፣ ውስጣዊው ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ አንታክትም፤ ውጫዊው ሰውነታችን እየመነመነ ቢሄድ እንኳን፥ ውስጣዊው ሰውነታችን በየዕለቱ ይታደሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ አንሰልች፤ በውጭ ያለው ሰውነታችን ያረጃልና፤ በውስጥ ያለው ሰውነታችን ግን ዘወትር ይታደሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል። |
መልካሙንና ደስ የሚያሰኘውን ፍጹም የሆነውንም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ እንድትችሉ አእምሮአችሁን በማደስ ሕይወታችሁ ይለወጥ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉት።
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ፤ ለጌታ ሥራ የምትደክሙት በከንቱ አለመሆኑን ዐውቃችሁ፥ ሳታቋርጡ ዘወትር የጌታን ሥራ ለመሥራት ትጉ።
ስለ እናንተ እንኳን ገንዘቤን ራሴንም አሳልፌ ብሰጥ እጅግ በጣም ደስ ይለኛል፤ ታዲያ፥ እኔ ይህን ያኽል አብዝቼ ስወዳችሁ እናንተ የምትወዱኝ እንዲህ በጥቂቱ ነውን?
እኛ በሠራነው የጽድቅ ሥራ ሳይሆን ራሱ በምሕረቱ አዳነን፤ ያዳነንም በአዲስ ልደት መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በተገኘው መታደስ ነው።
ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ በከበረና በማይጠፋው ጌጥ በገርነትና በጭምትነት መንፈስ ያጌጠው፥ በልብ ተሰውሮ የሚገኘው፥ ውስጣዊ ሰውነት ይሁን።