2 ቆሮንቶስ 13:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በእኔ ዐድሮ የሚናገረው ክርስቶስ መሆኑን ለማረጋገጥ ትፈልጋላችሁ፤ በእናንተ ዘንድ የሚታየውም የእርሱ ኀይል ነው እንጂ ድካሙ አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም የሚሆነው ክርስቶስ በእኔ ዐድሮ እንደሚናገር ማስረጃ በመፈለጋችሁ ነው። እርሱም በመካከላችሁ ብርቱ እንጂ ደካማ አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንንም የምለው ክርስቶስ በእኔ አድሮ እንደሆነ ማስረጃ በመፈለጋችሁ ነው፤ ክርስቶስ ስለ እናንተ አይደክምም፤ ነገር ግን በመካከላችሁ ኀያል ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክርስቶስ በእኔ አድሮ እንደሚናገር ማስረጃ ትሻላችሁና፤ እርሱም ሁሉ የሚቻለው ነው እንጂ፥ በእናንተ ዘንድ የሚሳነው የለም። |
እኔ ጳውሎስ በእናንተ ፊት ሳለሁ ትሑት ተባልኩ፤ ከእናንተ ስርቅ ግን በእናንተ ላይ ደፋር ተባልኩ፤ በክርስቶስ ቸርነትና ደግነት እለምናችኋለሁ፤
እኔ እውነተኛ ሐዋርያ መሆኔን የሚያስረዱት ነገሮች እኔ በመካከላችሁ ሳለሁ በትዕግሥት የፈጸምኳቸው ሥራዎች ናቸው፤ እነዚህም ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች ተአምራትም ናቸው።
እናንተ ይቅርታ ለምታደርጉለት ሰው እኔም ይቅርታ አደርግለታለሁ፤ ይቅር የምልለት በደል ካለ እኔ በክርስቶስ ፊት ይቅርታ የማደርግለት ስለ እናንተ ብዬ ነው።