ከእኔ በፊት የሕዝብ ገዢ ሆኖ የተሾመው ሁሉ በሕዝቡ ላይ ከባድ ሸክም በመሆን፥ በየቀኑ ለምግብና ለመጠጥ የሚሆን አርባ ብር ያስከፍላቸው ነበር፤ የገዢዎቹም አገልጋዮች እንኳ በሕዝቡ ላይ ሠልጥነውባቸው ይጨቊኑአቸው ነበር፤ እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለምፈራ እንደዚያ አላደረግሁም።
2 ቆሮንቶስ 11:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእናንተ ጋር ሳለሁ ችግር በደረሰብኝ ጊዜ ከመቄዶንያ የመጡ ወንድሞች በሚያስፈልገኝ ነገር ሁሉ ይረዱኝ ስለ ነበር በማንም ሸክም አልሆንኩም፤ እስከ አሁን በእናንተ ላይ በምንም ነገር ሸክም አልሆንኩም፤ ለወደፊትም ሸክም አልሆንባችሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእናንተም ጋራ ሳለሁ አንዳች ባስፈለገኝ ጊዜ፣ ከመቄዶንያ የመጡ ወንድሞች የሚያስፈልገኝን ስለ ሰጡኝ ለማንም ሸክም አልሆንሁም። በእናንተ ላይ በምንም ነገር ሸክም እንዳልሆን ተጠንቅቄአለሁ፤ ወደ ፊትም እጠነቀቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእናንተም ጋር እያለሁ በሚጎድለኝ ጊዜ፥ ከመቄዶንያ የመጡት ወንድሞች የጎደለኝን በሙሉ ስላሟሉልኝ፥ በማንም ላይ ሸክም አልሆንኩም፤ በማንኛውም መንገድ በእናንተ ላይ ሸክም እንዳልሆን ተጠንቅቄአለሁ፤ እጠነቀቅማለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናንተ ዘንድ በነበርሁበት ጊዜም፥ ስቸገር ገንዘባችሁን አልተመኘሁም። ባልበቃኝም ጊዜ ወንድሞቻችን ከመቄዶንያ መጥተው አሙአሉልኝ፤ በእናንተም ላይ እንዳልከብድባችሁ በሁሉ ተጠነቀቅሁ፤ ወደ ፊትም እጠነቀቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናንተም ጋር ሳለሁ በጎደለኝ ጊዜ፥ በማንም አልከበድሁበትም፤ ከመቄዶንያ የመጡት ወንድሞች የጎደለኝን በሙሉ ሰጥተዋልና፤ በነገርም ሁሉ እንዳልከብድባችሁ ተጠነቀቅሁ እጠነቀቅማለሁ። |
ከእኔ በፊት የሕዝብ ገዢ ሆኖ የተሾመው ሁሉ በሕዝቡ ላይ ከባድ ሸክም በመሆን፥ በየቀኑ ለምግብና ለመጠጥ የሚሆን አርባ ብር ያስከፍላቸው ነበር፤ የገዢዎቹም አገልጋዮች እንኳ በሕዝቡ ላይ ሠልጥነውባቸው ይጨቊኑአቸው ነበር፤ እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለምፈራ እንደዚያ አላደረግሁም።
ሲላስና ጢሞቴዎስ ከመቄዶንያ በመጡ ጊዜ ጳውሎስ “ኢየሱስ መሲሕ ነው” በማለት ለአይሁድ በትጋት እየመሰከረ በማስተማር ጊዜውን ሁሉ ያሳልፍ ነበር።
በእስጢፋኖስና በፈርዶናጥስ በአካይቆስም ወደ እኔ መምጣት ደስ ብሎኛል፤ እናንተ ከእኔ ጋር ባለመገኘታችሁ እነርሱ በእናንተ ምትክ የጐደለኝን አሟልተውልኛል።
ይህ የምትፈጽሙት የልግሥና አገልግሎት የክርስቲያኖችን ችግር ከማስወገዱም በላይ ሰዎች ለእግዚአብሔር ብዙ ምስጋና እንዲያቀርቡ ያደርጋቸዋል።
እንዲሁም እኔን በሚያስፈልገኝ ሁሉ እንዲረዳኝ ልካችሁት የነበረውን ወንድሜን ኤጳፍሮዲቱስን ወደ እናንተ መላክ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፤ እርሱ ከእኔ ጋር የተሰለፈ ወታደርና የሥራ ጓደኛዬ ሆኖ ሲሠራ የቈየ ነው።
ወንድሞች ሆይ! እንዴት እንደ ሠራንና እንደ ደከምን ታውቃላችሁ፤ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ በምናበሥርበት ጊዜ በአንዳችሁም ላይ ሸክም እንዳንሆን ሌሊትና ቀን በመሥራት እንደክም ነበር።