ነገር ግን እዚህ ድረስ መጥቼ በዐይኔ እስካየው ድረስ የተነገረኝን ሁሉ አላመንኩም ነበር፤ በጆሮዬ የሰማሁት በዐይኔ ያየሁትን እኩሌታ እንኳ አይሆንም፤ በእርግጥም ጥበብህና ሀብትህ በአገሬ ሳለሁ ከተነገረኝ በጣም ይበልጣል።
2 ዜና መዋዕል 9:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ እዚህ መጥቼ ሁሉን ነገር በዐይኔ እስካየሁ ድረስ የተነገረኝን ሁሉ አላመንኩም ነበር፤ ታዲያ በጆሮዬ የሰማሁት በዐይኔ ያየሁትን እኩሌታ እንኳ አልሆነም፤ በእርግጥም ጥበብህ ከተነገረኝ በጣም ይበልጣል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ መጥቼ የነገሩኝን በዐይኔ እስካይ ድረስ አላመንሁም ነበር፤ በርግጥም የጥበብህ ታላቅነት እኩሌታው እንኳ አልተነገረኝም፤ እኔ ከሰማሁት ዝና እጅግ ይልቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ግን መጥቼ በዓይኔ እስካየሁ ድረስ የነገሩኝን አላመንሁም፤ እነሆ፥ የጥበብህን ታላቅነት እኩሌታ አልነገሩኝም፤ ከሰማሁት ዝና ትበልጣለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ግን መጥቼ በዐይኔ እስካየሁ ድረስ የነገሩኝን አላመንሁም፤ እነሆ፥ የጥበብህን ታላቅነት እኩሌታ አልነገሩኝም፤ በሀገሬ ከሰማሁትም ዝና ይልቅ ጨመርህልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ግን መጥቼ በዐይኔ እስካየሁ ድረስ የነገሩኝን አላመንሁም፤ እነሆ፥ የጥበብህን ታላቅነት እኵሌታ አልነገሩኝም፤ ከሰማሁት ዝና ትበልጣለህ። |
ነገር ግን እዚህ ድረስ መጥቼ በዐይኔ እስካየው ድረስ የተነገረኝን ሁሉ አላመንኩም ነበር፤ በጆሮዬ የሰማሁት በዐይኔ ያየሁትን እኩሌታ እንኳ አይሆንም፤ በእርግጥም ጥበብህና ሀብትህ በአገሬ ሳለሁ ከተነገረኝ በጣም ይበልጣል።
እርሱ ከሰዎች ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ጥበበኛ ነበረ፤ ከኤዝራሐዊው ኤታን፥ የማሖል ልጆች ከሆኑት ከሄማን፥ ከካልኮልና ከዳርዓዕ የሚበልጥ ጥበበኛ ነበረ፤ ዝናውም ከፍ ብሎ በጐረቤት ሕዝቦች ሁሉ ዘንድ አስተጋባ፤
ይሁን እንጂ መጽሐፍ፥ “የሰው ዐይን ያላየውን፥ የሰው ጆሮ ያልሰማውን፥ የሰው ልብ ያላሰበውን፥ እግዚአብሔር ለሚወዱት አዘጋጅቶአል” ይላል።
ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ወደፊት ምን እንደምንሆንም ገና አልታወቀም፤ ነገር ግን ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እውነተኛ መልኩን ስለምናይ እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን።