የእግዚአብሔር መንፈስ የሠላሳዎቹ መሪ በሆነው በዐማሳይ ላይ ወረደ፤ እርሱም፦ “ዳዊት ሆይ! እኛ የአንተ ነን! የእሴይ ልጅ ዳዊት ሆይ! እኛ ከአንተ ጋር ነን! ለአንተና አንተን ለሚረዱ ሁሉ ሰላም ይሁን! እግዚአብሔር ከአንተ ጋር በመሆን ይረዳሃል፤” በማለት ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ፤ ዳዊትም እነርሱን በደስታ ተቀብሎ በሠራዊቱ ውስጥ አለቆች አደረጋቸው።
2 ዜና መዋዕል 26:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍልስጥኤማውያንን፥ በጒርባዓል ይኖሩ የነበሩትን ዐረቦችና መዑናውያንን ድል እንዲያደርግ እግዚአብሔር ረዳው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያን፣ በጉርበኣል በሚኖሩ ዐረቦችና በምዑናውያን ላይ ድልን አቀዳጀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያንና በጉርበኣል በሚኖሩ ዓረባውያን በምዑናውያንም ላይ ረዳው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያንና በዓለት ላይ በሚኖሩ ዓረባውያን፥ በምዕዑናውያንም ላይ አጸናው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያንና በጉርበኣል በሚኖሩ ዓረባውያን በምዑናውያንም ላይ ረዳው። |
የእግዚአብሔር መንፈስ የሠላሳዎቹ መሪ በሆነው በዐማሳይ ላይ ወረደ፤ እርሱም፦ “ዳዊት ሆይ! እኛ የአንተ ነን! የእሴይ ልጅ ዳዊት ሆይ! እኛ ከአንተ ጋር ነን! ለአንተና አንተን ለሚረዱ ሁሉ ሰላም ይሁን! እግዚአብሔር ከአንተ ጋር በመሆን ይረዳሃል፤” በማለት ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ፤ ዳዊትም እነርሱን በደስታ ተቀብሎ በሠራዊቱ ውስጥ አለቆች አደረጋቸው።
በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመነ መንግሥት ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች ወደ ገራር ሄደው በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ድንኳንና ጎጆ ሁሉ አፈራረሱ፤ የካምን ነገዶችና መዑናውያንንም ፈጽመው ፈጁአቸው ለበጎቻቸው ብዙ የግጦሽ ቦታ ስላገኙም ሕዝቡን አባረው ለዘለቄታው እዚያው መኖር ጀመሩ።
እምነታቸውንም በእግዚአብሔር አድርገው እርሱ እንዲረዳቸው ተማጠኑት፤ እግዚአብሔርም ጸሎታቸውን ሰምቶ፥ በሀጋራውያንና በእነርሱም የጦር ጓደኞች ላይ ድልን አጐናጸፋቸው፤
ጦርነቱ እግዚአብሔር የፈቀደው ስለ ነበረ፥ ከጠላት ወገን ብዙ ሰዎችን ገደሉ፤ እነርሱም ራሳቸው ተማርከው እስከ ተወሰዱበት ጊዜ ድረስ በምድሪቱ ላይ መኖራቸውን ቀጠሉ።
በዚህ ጊዜ አሳ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፥ ኀያላኑንም ሠራዊት ሆነ ደካማውንም የመርዳት ችሎታ አለህ፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፥ በአንተ ስለ ተማመንን እነሆ፥ ይህን ብዙ ሠራዊት ለመውጋት መጥተናልና እባክህ እርዳን፤ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ አምላካችን ነህ፤ አንተን ማሸነፍ የሚችል ማንም የለም።”
ከፍልስጥኤማውያን አንዳንዶቹ ብዙ ብርና ሌላም ዐይነት ስጦታ ለንጉሥ ኢዮሣፍጥ ሲያበረክቱ፥ አንዳንድ ዐረቦች ደግሞ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ በጎችና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ፍየሎች አመጡለት፤
በባሕር ዳርቻ ሰፍረው በነበሩት ኢትዮጵያውያን አጠገብ ፍልስጥኤማውያንና ዐረቦች ይኖሩ ነበር፤ እግዚአብሔርም እነርሱን በኢዮራም ላይ ጦርነት እንዲያደርጉ አነሣሣቸው፤
“አንተ በዚህ በምታደርገው ጦርነት የእስራኤል ወታደሮች ድጋፍ ይሆኑኛል ብለህ ታስብ ይሆናል፤ ነገር ግን አሸናፊም ሆነ ተሸናፊ እንድትሆን የሚያደርግህ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ እነሆ አሁንም እርሱ በጠላቶችህ ድል እንድትሆን ያደርግሃል።”
የፍልስጥኤም ሕዝብ ሆይ! እነሆ የተደበደባችሁበት በትር ተሰበረ፤ ሆኖም ደስ ሊላችሁ አይገባም፤ አንድ እባብ በሞተ ጊዜ ሌላ ከእርሱ የባሰ በቦታው ይተካል፤ ከእባብ ዕንቊላል በክንፍ የሚበር እሳት የመሰለ ዘንዶ ይፈለፈላል።
እስከ ዛሬ ድረስ የእግዚአብሔር ርዳታ አልተለየኝም፤ ስለዚህ ለትንሹም ለትልቁም እየመሰከርኩ እዚህ ቆሜአለሁ፤ ነቢያትና ሙሴ አስቀድመው እንዲህ ይሆናል ያሉትን ከመናገር በቀር ሌላ ምንም አልተናገርኩም።