Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 20:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከዚህ በኋላ የዐሞንና የሞአብ ሠራዊት ከእነርሱም ጋር የጦር ቃል ኪዳን ጓደኞቻቸው የሆኑት መዑናውያን ኢዮሣፍጥን ለመዋጋት መጡ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከዚህ በኋላ ሞዓባውያንና አሞናውያን ከጥቂት ምዑናውያን ጋራ ሆነው ኢዮሣፍጥን ለመውጋት መጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እንዲህም ሆነ፤ ከዚህ በኋላ የሞዓብና የአሞን ልጆች ከእነርሱም ጋር ምዑናውያን ኢዮሣፍጥን ሊወጉ መጡ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከዚህ በኋላ የሞ​ዓ​ብና የአ​ሞን ልጆች ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ምዑ​ና​ው​ያን ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን ሊወጉ መጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እንዲህም ሆነ፤ ከዚህ በኋላ የሞዓብና የአሞን ልጆች ከእነርሱም ጋር ምዑናውያን ኢዮሳፍጥን ሊወጉ መጡ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 20:1
15 Referencias Cruzadas  

በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመነ መንግሥት ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች ወደ ገራር ሄደው በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ድንኳንና ጎጆ ሁሉ አፈራረሱ፤ የካምን ነገዶችና መዑናውያንንም ፈጽመው ፈጁአቸው ለበጎቻቸው ብዙ የግጦሽ ቦታ ስላገኙም ሕዝቡን አባረው ለዘለቄታው እዚያው መኖር ጀመሩ።


ንጉሥ አሳ ታላላቅ ጋሻና ጦር የታጠቁ ሦስት መቶ ሺህ ሠራዊት ከይሁዳ፥ ታናናሽ ጋሻና ቀስት የያዙ ሁለት መቶ ሰማኒያ ሺህ ሠራዊት ከብንያም ነበሩት፤ እነዚህ ሁሉ በሚገባ የሠለጠኑ ጀግኖች ወታደሮች ነበሩ።


በመንፈሳዊ ጉዳይ ሁሉ ወሳኝ ሥልጣን የሚኖረው ሊቀ ካህናቱ አማርያ ነው፤ በሌላው ጉዳይ ሁሉ ወሳኝ ሥልጣን የሚኖረው የይሁዳ አስተዳዳሪ የሆነው የእስማኤል ልጅ ዘባድያ ነው፤ ሌዋውያን በፊታችሁ እንደ ባለሥልጣን ሆነው ያገለግላሉ፤ ያለ ፍርሀት በድፍረት ሥሩ! እግዚአብሔርም መልካም ሥራ ከሚሠሩት ጋር ይሁን!”


የሐናኒ ልጅ የሆነው ኢዩ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ለመገናኘት መጥቶ እንዲህ ሲል ገሠጸው፤ “አንተ ክፉዎችን መርዳትና እግዚአብሔርን ከሚጠሉት ጋር መተባበር መልካም ይመስልሃልን? ይህ ያደረግኸው ክፉ ነገር የእግዚአብሔር ቊጣ በአንተ ላይ እንዲወርድ አድርጎአል፤


በተመሸጉት በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ዳኞችን ሾሞአል፤


“እነሆ አሁን የዐሞን፥ የሞአብና የኤዶም ሕዝቦችን ተመልከት፤ አደጋ ጥለውብናል፤ የቀድሞ አባቶቻችን ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ ወደነዚህ ሕዝቦች ግዛቶች እንዲገቡ አልፈቀድክላቸውም፤ የቀድሞ አባቶቻችን እነርሱን ዞረው አለፉ እንጂ አላጠፉአቸውም፤


ፍልስጥኤማውያንን፥ በጒርባዓል ይኖሩ የነበሩትን ዐረቦችና መዑናውያንን ድል እንዲያደርግ እግዚአብሔር ረዳው።


ንጉሥ ሕዝቅያስ እግዚአብሔርን በታማኝነት በማገልገል ብዙ ነገሮችን ካከናወነ በኋላ፥ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ሰናክሬም ይሁዳን ወረረ፤ እንደሚያሸንፍ ተማምኖ የተመሸጉትን ከተሞች ከበበ


የይሁዳ ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፦ “የሞአብ ሕዝብ ምን ያኽል ኩራተኛ መሆኑን፥ ትዕቢተኛነቱን፥ ዕብሪተኛነቱንና ንቀቱን ሰምተናል፤ ነገር ግን ፉከራው ሁሉ ከንቱ ነው።”


ከዖዝያን ልጅ ከኢዮአታም የተወለደው አካዝ በይሁዳ በነገሠበት ዘመን፥ የሶርያ ንጉሥ ረጺንና የእስራኤል ንጉሥ የረማልያ ልጅ ፋቁሔ ጦርነት ማስነሣት ፈልገው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ ነገር ግን ኢየሩሳሌምን ድል ሊያደርጉአት አልቻሉም።


እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ትክክለኛ ፈራጅ እንደ መሆንህ ገሥጸን፤ ነገር ግን ፈጽመን እንዳንጠፋ በምትቈጣበት ጊዜ አይሁን።


እግዚአብሔር ስለ ዐሞን እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል ወንዶች ልጆች የሉትምን? ወራሾች የሉትምን? ታዲያ ሚልኮም የተባለውን ጣዖት የሚያመልኩ ወገኖች የጋድን ነገድ አስለቅቀው በከተሞቹ የሰፈሩት ለምንድን ነው?


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸዋለሁም፤ ስለዚህ ትጋ፤ ንስሓም ግባ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos