1 ጢሞቴዎስ 6:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዳንዶች እንዲህ ዐይነቱ ዕውቀት አለን በማለት ከእምነት መንገድ ወጥተዋል። የእግዚአብሔር ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዚህ ዐይነት ዕውቀት አለን ሲሉ የነበሩ አንዳንዶች ከእምነት ስተዋል። ጸጋ ከእናንተ ጋራ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንዳንዶች እንዲህ ዓይነቱ እውቀት አለን በማለት የእምነትን መንገድ ስተዋል። ጸጋ ከአንተ ጋር ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ እውቀት አለን ብለው አንዳንዶች ስለ እምነት ስተዋልና። ጸጋ ከአንተ ጋር ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ እውቀት አለን ብለው፥ አንዳንዶች ስለ እምነት ስተዋልና። ጸጋ ከአንተ ጋር ይሁን። |
ስለዚህ በሮም ለምትኖሩ፥ እግዚአብሔር ለወደዳችሁና ወገኖቹ እንድትሆኑ ለጠራችሁ ሁሉ፦ ከአባታችን ከእግዚአብሔርና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
እኔንና በዚህ ያለውን መላ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስተናግደው ጋይዮስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ የከተማይቱ በጅሮንድ የሆነው ኤራስጦስ፥ ወንድማችንም ቋርጦስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። [
ከእኔ ጋር ያሉት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል፤ በእምነት ከእኛ ጋር ተካፋይ ለሆኑ ወዳጆቻችን ሁሉ ሰላምታ አቅርብልን። የእግዚአብሔር ጸጋ ከሁላችሁም ጋር ይሁን።